You are currently viewing በግፍ የተገደሉ የኪረሞ አማራዎችን አስከሬን በማንሳት ስርዓተ ቀብር ለመፈጸም የተደረገው ጥረት በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ምክንያት አለመሳካቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር13 ቀ…

በግፍ የተገደሉ የኪረሞ አማራዎችን አስከሬን በማንሳት ስርዓተ ቀብር ለመፈጸም የተደረገው ጥረት በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ምክንያት አለመሳካቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር13 ቀ…

በግፍ የተገደሉ የኪረሞ አማራዎችን አስከሬን በማንሳት ስርዓተ ቀብር ለመፈጸም የተደረገው ጥረት በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ምክንያት አለመሳካቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ኪረሞ ህዳር 11/2015 የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች በፈጸሙት ማንነት ተኮር ጥቃት 9 አማራዎች ተገድለዋል። በህዳር 9/2015 የተገደሉት ብዛት በትክክል ባይታቅም ህዳር 10/2015 ደግሞ ከ8 በላይ አማራዎችን መረሸናቸውም ይታወቃል። ህዳር 11/2015 በግፍ ከተገደሉት መካከልም:_ 1) መሀመድ ከማል (የ4 ልጆች አባት)፣ 2) ደሳለኝ ዳውድ እና 3) ካሳ ከበደ፣ 4) ኡስማን አሊ የተገደሉ ሲሆን 5) ዘመን የተባለ አማራ በ2013 ከኪረሞ ወረዳ ነጭሎ ቀበሌ በማንነታቸው ከተፈናቀሉት መካከል አንዱ ነው። 2 ዓመት በሚሊሻነት አገልግሏል። ህዳር 11/2015 ከቆቆፌ ቀበሌ በጥበቃ ላይ የነበሩ ሚሊሾችን ኑ ተሎ በሚል ወደ ኪረሞ ከወሰዱ በኋላ በስለት ገድለውታል፤ ክህደትም ፈጽመዋል። 6) ካሳሁን አብዬ፣ 7) ቄስ ስመኘው ዘውዱ፣ 8 አስቻለው ይሁኔ እና 9) አዲሱ ሞንጋሴ የተባሉ ነዋሪዎች ይገኙበታል። መሀመድ ቁሜ የተባለ አማራም ቀደም ሲል እንደሞተ የተገለጸ ቢሆንም ተሸክመው ወደ ሀሮ አዲስ ዓለም የወሰዱት መሆናቸውንና ሩሁ (ነፍሱ) እንዳልወጣ ተነግሯል። ቤተሰብ በሟቾች የእጅ ስልክ ላይ በሚደውሉበት ወቅት ስልኩን የሚያነሱ ሰዎችን “እናንተ እነማን ናችሁ? ሸኔ ወይስ ልዩ ኃይል?” በማለት ገዳዮችን ሲጠይቁ አንዱ “ሸኔም ሆነ ልዩ ኃይል ያው ኦሮሞ ነው!” የሚል ምላሽ ስለመስጠቱ ተመላክቷል። አማራዎች ከሀሮ አዲስ ዓለም ተነስተው ህዳር 12/2015 አስከሬን አንስተው ወግ እና ባህሉ በሚፈቅደው መሰረት አፈር ለማልበስ ወደ ኪረሞ ቢያቀኑም የቡድን መሳሪያ በእያቅጣጫው ያጠመደው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ባለመፍቀዱ እና ወደ ከፋ ግጭት ላለመግባት ሲሉ ስርዓተ ቀብር ለመፈፀም አለመቻላቸው ተነግሯል። አሁንም በኪረሞ አካባቢ ያሉ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትም ከኦነግ ሸኔ አባላት ጋር በመስማማት ተጨማሪ ኃይል ይዘው በመዝመት በኪረሞ፣በሀሮ አዲስ ዓለም እና በጃርዴጋ ሊዘምቱ ስለመሆኑ መረጃ ደርሶናል የሚሉት የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ከህዳር 9 እስከ 11/2015 የተገደሉት አማራዎች ቁጥር ከዚህ እንደሚያሻቅብ ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply