
“በጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት የተሸነፈው ብልፅግና አዋኪ የጥይት ተኩስ የሚፈፅሙ ቅጥረኞችን በማሰማራት ህዝባችን እየረበሸ ይገኛል።” የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 2/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በህገ ወጥነት በኦህዴድ ፍላጎት አላግባብ ወደ አማራ ክልል የዘመተው ሰራዊት በማዕበላዊ ህዝባዊ እምቢተኝነት ዕኩይ ተልዕኮው ተመክቶ ከስምሪቱ አፈግፍጎ እንዲወጣ የተስማማ ቢሆንም አዋኪ የጥይት ተኩስ የሚፈፅሙ ቅጥረኞችን በማሰማራት ህዝባችን እያወከ መሆኑን እያሳወቅን ህዝባችን ይህን ድርጊት የሚፈፅሙትን ለይቶ እንዲታገላቸውና በየአካባቢው ለሚገኝ የፋኖ መዋቅር እንዲጠቁም እናሳስባለን። አዋኪ ቅጥረኞቹ የመንግስት የጦር መሳሪያን ተጠቅመው በግፍ በታደላቸው የተተኳሽ ጥይት የህዝባችን ሰላም የሚረብሹት የተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮችን በመልበስም ጭምር ነው። በተለይ የልዩ ሀይል፣ የሚሊሽያ ፣የአድማ በታኝ የተደንብ ልብስ የሚለብሱና ተሽከርካሪ ተመድቦላቸው እየዞሩ የጥይት ተኩስ የሚፈፅሙ አካላትን በንቃት በመከታተል ዕኩይ ዓላማቸውን ልናከሽፍ ይገባል። የቅጥረኞቹ ዋና ዓላማ ህዝቡን በማማረር ጨፍላቂና ጨፍጫፊ የፌዴራል ሰራዊት በከተማው ተመልሶ እንዲሰማራ በማድረግ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ማዳከም ወይም ካልተሳካ ተቃዎሞናል የሚሉትን ህዝብ በሁከት የመበቀል ስትራቴጂን እየተገበሩ መሆኑን ተገንዝቦ አካባቢያችንን ከቅጥረኞች ረብሻ እንድንጠብቅ እናሳስባለን። አንድነት ሀይል ነው!!
Source: Link to the Post