በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት ለወራት በእስር ላይ የሚገኙት እነ ፋኖ ሰለሞን አጠናው አቃቢ ህግ በተደጋጋሚ ቀጠሮ አሟልቶ ምስክሮቹን ባለማቅረቡ አላግባብ የፍትህ ሂደቱ እየተንዛዛባቸው መሆኑን በ…

በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት ለወራት በእስር ላይ የሚገኙት እነ ፋኖ ሰለሞን አጠናው አቃቢ ህግ በተደጋጋሚ ቀጠሮ አሟልቶ ምስክሮቹን ባለማቅረቡ አላግባብ የፍትህ ሂደቱ እየተንዛዛባቸው መሆኑን በመጥቀስ ተቃወሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት ለወራት በእስር ላይ የሚገኙት እነ ፋኖ ሰለሞን አጠናው በጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ዛሬ ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ቀደም ሲል በተሰጣቸው ቀጠሮ መሰረት ቀርበዋል። መዝገቡ የሚጠራው በፋኖ መሪው በሰለሞን አጠናው ሲሆን ሰለሞን አጠናውን ጨምሮ ሰለሞን ፀሀይ፣ሚናስ አለማየሁ እና ናሁሰናይ አንዳርጌ 4ቱ በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት ሆነው እየተከታተሉ ሲሆን 4ቱ ግን በዋስ ወጥተው በውጭ ሆነው እየተከራከሩ መሆኑ ተጠቅሷል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል የፋኖዎችን ጠበቃ ታዬ ብርሀኑን ያነጋገረ ሲሆን የዛሬው መዝገብ ተቀጥሮ የነበረው አቃቢ ህግ ምስክሮችን አቅርቦ እንዲያሰማ ነበር። አቃቢ ህግ 28 ምስክሮች እንዳሉት መግለፁና ከአሁን ቀደም በነበሩት ቀጠሮዎች 1 እና 2 ምስክሮችን ሲያመጣ ነበር። በተከሳሾች በኩል አቃቢ ህግ ምስክሮችን አሟልቶ ይቅረብ በማለታቸው መዝገቡ ከ4 ጊዜ በላይ መቀጠሩ ተጠቅሷል። ይሁን እንጅ አቃቢ ህግ ከ4 ጊዜ በላይ ምስክሮችን አሟልቶ ይዞ ባለመቅረቡ በተከሳሽ ፋኖዎች ዘንድ በረዣዥም ቀጠሮ ምክንያት ተጉላላን በሚል ቅሬታ ስለመቅረቡ ተነግሯል። መፍትሄ ለሌለው ጉዳይ መመላለሱ ትርጉም የለውም በማለት ፍ/ቤቱ ለአንድ ዓመት መቅጠር ይችላል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። የተከሰሱበት ወንጀልም “የክፉ አድራጊዎች” አባል መሆን፣ ተቋም መድፈርና እስረኛ ማስፈታት የሚል እንደሆነ ጠበቃ ታዬ ተናግረዋል። ጠበቃ ታዬ ተከሳሾች ቢፈረድባቸው እንኳ ታስረው ጨርሰውታል ብለዋል። በጠበቃ በኩልም አቃቢ ህግ ምስክሮችን ማቅረብ እየቻለ ባለመሆኑ መዝገቡ ይቋረጥልን፤ አቃቢ ህግም ምስክሮችን ባገኘ ጊዜ ሂደቱን ማስቀጠል ይችላል በሚል ለችሎቱ ጥያቄ ቀርቧል። ችሎቱም ምስክሮቹ የፀጥታ አካላት በመሆናቸው ከወቅቱ አኳያ ተጨማሪ አንድ ቀጠሮ ብሰጥ ይሻላል በሚል ለቀጣይ ህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ምስክሮችን ይዞ እንዱቀርብ ሲል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply