በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ 16 ፋኖዎች ላይ ከተመሰረቱት 14 ክሶች መካከል አቃቢ ህግ 4ቱን አሻሽሎ እንዲቀርብ ሲል የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።…

በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ 16 ፋኖዎች ላይ ከተመሰረቱት 14 ክሶች መካከል አቃቢ ህግ 4ቱን አሻሽሎ እንዲቀርብ ሲል የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።…

በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ 16 ፋኖዎች ላይ ከተመሰረቱት 14 ክሶች መካከል አቃቢ ህግ 4ቱን አሻሽሎ እንዲቀርብ ሲል የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ 16 ፋኖዎች ትናንት ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርበዋል። ፋኖዎቹ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ችሎት ቁጥር 21 ቀርበው በክሱ መቃወሚያ ላይ የተሰጠውን የፍ/ቤቱን ብይን ተከታትለዋል። በተጠርጣሪዎች ላይ አቃቢ ህግ 14 ክሶችን ያቀረበ መሆኑን የገለፁት ጠበቃ ታዬ ብርሀኑ ትናንት በነበረው ችሎት ፍ/ቤቱ መቃወሚያ ከቀረበባቸው ከ14ቱ ክሶች መካከል 4ቱ ተሻሽለው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል ብለዋል። በእነ ቻላቸው እንየው መዝገብ የአቃቢ ህግ ምስክር ለመስማትም ለታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዟል። በእነ ሰለሞን አጣናው መዝገብ ላይም ከሁለቱ ክስ አንዱን አሻሽሎ እንዲቀርብ በሚል ለህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን በሌላኛው 7 ተከሳሾች ያሉበት የሰለሞን አጣናው መዝገብ ደግሞ አቃቢ ህግ ካቀረባቸው ክሶች መካከል ሶስቱን አሻሽሎ እንዲቀርብ በማለት በተመሳሳይ ለህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ትዕዛዝ ተሰጥቷል ብለዋል። ተከሳሾች ለረዥም ጊዜ ነው የታሰርነው፤ ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን በሚል ቀጠሮው በረዘመ ቁጥር ላልተፈለገ መጉላላት እየተዳረጉ መሆናቸውን በመጥቀስ ከፍ ያለ ቅሬታ አቅርበዋል ነው የተባለው። በጠበቃ በኩል ተከሳሾች ክስ ሳይመሰረትባቸው ለወራት ያለፍትህ ታስረው ስለነበር ቅሬታቸው አግባብ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን በኮሮና ምክንያት ተደራራቢ መዝገቦች መኖራቸውን ታሳቢ አድርጎ ፍ/ቤቱ የሰጠውን ቀጠሮ ተገቢነትን እንደሚቀበሉት አስታውቀዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀልጣፋ ፍትህ እንዲያገኙና ክብራቸው በተጠበቀ መንገድ እየሰራ መሆኑን እንደሚገነዘቡ የተናገሩት ጠበቃ ታዬ ከችሎት መታደም ጋር ተያይዞ የክፍል ጥበት መኖሩና በፀጥታ አካላት ላይ አለመናበብ እንደሚስተዋል ጠቅሰው እንዲሻሻል አሳስበዋል። እንደአብነት እራሳቸውን ጠበቃ ታዬን ጨምሮ አናስገባም በሚል በፀጥታ አካላት ክልከላ ተደርጎባቸው እንደነበር አውስተው የችሎት ማስዋያው አዳራሽ ካለው የወንበር ውስንነት አኳያ ችሎት የሚታደሙ ቤተሰቦች ስም ዝርዝር ለፀጥታ አካላት ባለመተላለፉና በመናበብ ችግር በጅምላ ክልከላ የማድረግ ሁኔታ ይታያል፤ ይህ መስተካከል አለበት ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply