በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ ፋኖዎች ፍ/ቤት ቀርበው ቀሪ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለጥር 19 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 7…

በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ ፋኖዎች ፍ/ቤት ቀርበው ቀሪ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለጥር 19 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 7…

በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ ፋኖዎች ፍ/ቤት ቀርበው ቀሪ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለጥር 19 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከጠበቃ ታዬ ብርሀኑ ጋር የነበረን ቆይታ እንዳመለከተው እነ ፋኖ ሰለሞን አጠናው በዛሬው እለት ታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ቀርበዋል። በችሎት የቀረቡት ፋኖዎችም ሰለሞን አጠናው፣ዮሐንስ ንጉሱ፣ሚናስ አለማየሁ፣ናሁሰናይ አንዳርጌ፣ ቻሌ ግርማ፣ምህረት ያለው፣ሙሉቀን ቀለቤ፣ባበይ አበበ እና አለልኝ ገብሩ ስለመሆናቸው ጠበቃ ታዬ ተናግረዋል። አቃቢ ህግ አሉኝ ካላቸው 17 ምስክሮች መካከል 5ቱን አቅርቦ ማስመስከሩ ተገልጧል። ቀሪዎቹን የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ለመስማትም ለጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ነው ጠበቃ ታዬ ብርሀኑ የገለፁት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply