በጎንደር ከተማ ቁስቋም ሰፈር አካባቢ በፓትሮል የአካባቢውን የፀጥታ ሁኔታ በመቃኘት ላይ በነበሩ በልዩ ኃይል እና በፖሊስ አባላት ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በጎንደር ከተማ ቁስቋም ሰፈር አካባቢ በፓትሮል የአካባቢውን የፀጥታ ሁኔታ በመቃኘት ላይ በነበሩ በልዩ ኃይል እና በፖሊስ አባላት ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በጎንደር ከተማ ቁስቋም ሰፈር አካባቢ በፓትሮል የአካባቢውን የፀጥታ ሁኔታ በመቃኘት ላይ በነበሩ በልዩ ኃይል እና በፖሊስ አባላት ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር ከተማ ቁስቋም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የታጣቁ አካላት በፓትሮል የአካባቢውን የፀጥታ ሁኔታ በመቃኘት ላይ በነበሩ በልዩ ኃይል እና በፖሊስ አባላት ላይ በደፈጣ ጥቃት መፈፀማቸውን ያነጋገርናቸው የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል። በአንድ ፓትሮል ላይ በነበሩ የአማራ ልዩ ሀይል እና የፖሊስ አባላት ላይ በከፈቱት ድንገተኛ ተኩስም ከፀጥታ አካላት ህይወታቸው ያለፈና የቆሰሉ ስለመኖራቸው ተሰምቷል። የቆሰሉ የሰላምና ፀጥታ አስከባሪዎችም ወደ ጎንደር ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የዐይን እማኞች ተናግረዋል። በዛሬው እለት ከሰዓት በኋላ የተለያዩ የጎንደር ከተማ አመራሮች ስለ ህዝቡ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ስጋቶች ሁሉ ተነስተው ውይይት እንደተደረገባቸው ለማወቅ ተችሏል። በጎንደር ከተማ ቁስቋም ሰፈር ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽት 2 ሰዓት አካባቢ ስለነበረው ተኩስና ስለደረሰው ጉዳት ለማጣራት በሚል ለጎንደር ከተማ ፖሊስ አዛዥ ለኮማንደር አየልኝና ለከተማው ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ለአቶ አንደበት በተደጋጋሚ ብንደውልም የሚጠራ ስልካቸው ባለመነሳቱ ሀሳባቸውን ለማካተት አልተቻለም። ኮማንደር አየልኝ ቆየት ብለው “መረጃ እንዲሰጡን በሚል የደወልን መሆኑን አውቀው ስልክ እንዲያነሱ ለጻፍንላቸው የፁሁፍ መልዕክት” “ይቅርታ ስራ ላይ ሆኜ ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። መኪና ላይ እያሉ የደፈጣ ተኩስ ከተከፈተባቸው የፀጥታ አካላት መካከል ህይወታቸው ያለፈና የቆሰሉ ስለመኖራቸው ከነዋሪዎች በደረሰን መረጃ ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት በፁሁፍ ጠይቀናል፤ ነገር ግን አዛዡ ምላሽ አልሰጡበትም። በአንጻሩ በጎንደር ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞላ መልካሙ በቁስቋምና በጎሀ መሀል ላይ ተኩስ እንደነበር ገልፀው እንዲህ ዓይነት መረጃዎችን ሀላፊነቱን ወስዶ ኦፊሻሊ መግለፅ ያለበት አካል ስላለ እሱ ቢሰጥበት እንደሚሻል ጠቁመዋል። የጎንደር ከተማ የፀጥታ አመራሮች ጉዳዩን በተመለከተ እየገመገሙ ስለመሆናቸውና ሲጨርሱ መረጃ ሊሰጡ እንደሚችሉ ነው አቶ መልካሙ የተናገሩት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply