You are currently viewing በጎንደር ከተማ በተካሄደው የመንፈሳዊ ሩጫ ውድድር የፋኖ አርበኛ ቻላቸው እንየው ልጅ አሸነፈች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ታህሳስ 16 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ…

በጎንደር ከተማ በተካሄደው የመንፈሳዊ ሩጫ ውድድር የፋኖ አርበኛ ቻላቸው እንየው ልጅ አሸነፈች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ…

በጎንደር ከተማ በተካሄደው የመንፈሳዊ ሩጫ ውድድር የፋኖ አርበኛ ቻላቸው እንየው ልጅ አሸነፈች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በህወኃት ወረራ ወቅት ብዙ ጀብጆችን ሰርቶ በክብር የተሰዋው የአርበኛ ፋኖ ቻላቸው እንየው ልጅ የሆነችው ማህሌት ቻላቸው እንየው ሩጫውን በአንደኝነት ጨርሳለች። መፅሐፍ ቅዱስ እና የ7,000 ብር ተሸላሚም ሁናለች። አባቷ ፋኖ ቻላቸው እንዬው በህልውና ዘመቻው ደብረ ዘቢጥ ላይ በተደረገው ውጊያ ጀብዱ ፈጽሞ የተሰዋ ጀግና ነበር። አርበኛ ቻላቸው እንዬውን ሲያስሩት፣ ሲፈቱት፣ ሲያንገላቱት፣ ህክምና እየከለከሉ ሲሰቃዩት ቢቆዩም አገር ስትወረር ጦርነቱ ሲጀምር ግን ግምባር ቀደም ተሰላፊ ሆኖ “እኔስ ሄድኩላችሁ ይብላኝ ለከራሚ” የሚመስል አሟሟት ነው የሞተው። በ2008 ዓ.ም ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ በጠላት ሲከበብ ቀድሞ የደረሰው ይኸው ጀግና አርበኛ ፋኖ ቻላቸው እንዬው እንደነበር ታላቅ ወንድሙ አርበኛ ገበየሁ እንዬው መናገራቸው ይታወሳል። አሻራ ሚዲያ እንደዘገበው። ፎቶ:-ታደለ ጥበቡ

Source: Link to the Post

Leave a Reply