በጎንደር ከተማ ታስሮ ምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ገንዳ ውሃ ከተማ ፖሊስ ባለማቅረቡ በጠበቃ በኩል ክሱን ሲከታተል የቆየው የፋኖ ብርሀኑ ነጋ መዝገብ መዘጋቱ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማ…

በጎንደር ከተማ ታስሮ ምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ገንዳ ውሃ ከተማ ፖሊስ ባለማቅረቡ በጠበቃ በኩል ክሱን ሲከታተል የቆየው የፋኖ ብርሀኑ ነጋ መዝገብ መዘጋቱ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማ…

በጎንደር ከተማ ታስሮ ምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ገንዳ ውሃ ከተማ ፖሊስ ባለማቅረቡ በጠበቃ በኩል ክሱን ሲከታተል የቆየው የፋኖ ብርሀኑ ነጋ መዝገብ መዘጋቱ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ስለአማራ ህዝብ ማንነት የሚታገለው ፋኖ አርበኛ ብርሃኑ ነጋ ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በገንዳ ውሃ፣ ከዛም ወደ ጎንደር ከተማ ተወስዶ በአንገረብ ማ/ቤት በአደራ እስረኛ መልክ ታስሮ እንደሚገኝ ይታወቃል። ፋኖ አርበኛ ብርሃኑ ነጋ በጭልጋ ወረዳ በአማራ ላይ በውክልና ጦርነት በትሕነግ አሽከሮች የሚፈፀመውን ጭፍጨፋ በመቃወም ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ጫካ የገባ መሆኑና በመጨረሻም ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅሎ በነበረበት ሁኔታ ነው በምዕራብ ጎንደር ዞን የግል ጥላቻ ባነገቡና ከትናንት ውድቀት ለመማር ባልፈቀዱ በውስን አመራሮች እንደታሰረ የተነገረው። ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በአደራ እስረኛ መልክ እስከ መቼ ነው የምታሰረው በሚል በዋስትና እንዲፈታ መጠየቁና ፍ/ቤቱም ጉዳይህ በተጠረጠርክበትና በተያዝክበት በምዕራብ ጎንደር ዞን መታየት ይችላል በማለት መዝገቡን ከወራት በፊት መዝጋቱ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ጉዳዩን የያዘው የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠርጣሪው ይቅረብ በሚል በተደጋጋሚ ለዞን ፖሊስ የሰጣቸው ቀጠሮዎች ተፈጻሚ ሳይሆኑ እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ተደርሷል። በዚህም ትናንት በነበረው ቀጠሮ እንደተለመደው ፖሊስ ልዩ ልዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ ባያቀርበውም በጠበቃ አስቴሮ በኩል ተከሳሹ ጉዳዩን ተከታትሏል። በእለቱ በምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ላይ በከሳሽ ከተከፈተበት የግድያና የዝርፊያ መዝገብን ነጻ በማለት የዘጋ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል። ይሁን እንጅ ጎንደር ላይ በጠቅላይ ፍ/ቤት በኩል የሱዳን ካምፕ አቃጥሏል በሚል ክስ ሳይመሰረትበት እንዳልቀረና ለዚህም ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ የተሰጠው ስለመሆኑ ነው ምንጮች የገለፁት። ስለ ጉዳዩ ለማጣራት በሚል ገንዘብ እየተከፈላቸው ጠበቃ ሆነው ቆመውለታል ለተባሉት ለአቶ አስቶሬ ብንደውልም በሂደት ላይ ያለ መዝገብ ነው በሚል መረጃ ለማጋራት አልፈቀዱም። ይሁን እንጅ የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሳሹ ይቅረብ በሚል ተደጋጋሚ ትዕዛዝ እየሰጠ መሆኑንና ፖሊስ በልዩ ልዩ ምክንያት እንዳላቀረበው ገልፀው ፍ/ቤቱ ምን እርምጃ ወሰደ ብን ስንጠይቃቸው አሁንም ነገሩን ሚስጥር አድርገውታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply