በጎንደር ከተማ አስተዳደር የማራኪ ክፍለ ከተማ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ የግል የጦር መሳሪያ ታጣቂዎችን አስመረቀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ…

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የማራኪ ክፍለ ከተማ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ የግል የጦር መሳሪያ ታጣቂዎችን አስመረቀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምርቃን ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማ አስተዳደሩ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አወቀ አስፈሬ እንደተናገሩት ጎንደርን ለማተራመስ የቋመጠውን ወራሪና አሸባሪ ኃይል ለመመከት የሚያስችል የክህሎትና የአመከላከት ስልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡ ጎንደር ከተማን ነሪዎች ከሀብት ማሰባሰብ ባሻገር በብሎክ አደረጃጀት የከተማዋን ሰላም በመጠበቅ እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም በተሰጠው ሰልጠና መሰራት የአካባቢውን ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ለማድረ ቸውም የበለጠ በኃላፊነት መንፈስ መሰራት ይጠበቅባችኃል ሲሉ አቶ አወቀ ተናግረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃለፊ አቶ ፋሲል ሰንደቁ አሸባሪው ቡድን የፈፀመብንን ወረራ ለመመከት የሀገራችን ህዝቦች ከጫፍ እስከ ጫፍ ተመዋል፤ በዚህም ድል እየተመዘገበ ነው ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ስልጠናውን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የተመረቃችሁ የግል የጦር መሳሪያ ታጣቂዎች የወሰዳችሁት ስልጠና የአካባቢውን ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ለማድረስ አጋዥ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡ ከሰልጣኞች መካከል ወጣት አለልኝ ደሴ ደግሞ አደረጃጀቱ ተፈጥሮ ስልጠናውን መውሰዳችን የአመለካከትና የክህሎት እውቀት እንዲኖረኝና የራስ መተማመን እዳዳብር አግዞኛል ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ሌለኛው ተመራቂ መርጌታ አጣናው አሰፋ ደግሞ አሸባሪ ቡድኑ እየፈፀመ ያለውን ግፍ ለመመከት በስልጠናው መሳተፋቸውን ገልፀዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፋፃሚ አቶ ፋሲል አብዬ በበኩላቸው ስልጠናው ከተማዋን የኢንዱስትሪ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማዕከል ሆና እንድትቀጥል የሚስችለውን ሰላም ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ስለመግለጻቸው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው የጎንደር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply