You are currently viewing በጎንደር ከተማ እና አካባቢው የሚስተዋል የእገታ ወንጀል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግለት ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ ከጎን…

በጎንደር ከተማ እና አካባቢው የሚስተዋል የእገታ ወንጀል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግለት ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከጎን…

በጎንደር ከተማ እና አካባቢው የሚስተዋል የእገታ ወንጀል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግለት ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከጎንደር ለአማራ ሚዲያ ማዕከል መረጃውን ያደረሱ ምንጫችን እንደሚሉት የእገታ ወንጀል በጭልጋ፣በመተማ፣ በአርማጭሆና በሌሎች የተለያዩ አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን ጎንደር ከተማ ድረስ እየተፈፀመ ነው። በአጋቾች ላይ ጠንከር ያለ እና የተባበረ እርምጃ እየተወሰደ ባለመሆኑ ዛሬ ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙ የእገታ ወንጀሎች አሳሳቢ ሆነዋል ይላሉ። ህጻናትንና ሴቶችን ሳይቀር በማገት ቤተሰብን በመቶ ሽህ የሚቆጠር ገንዘብ በመጠየቅ ማህበረሰቡን እያሳቀቁትና በኢኮኖሚ እያደቀቀቁት ይገኛሉ ይላሉ ሌላኛው የጎንደር ከተማ ምንጫችን። የከተማ አስተዳደሩም ሆነ አጠቃላይ የፀጥታ መዋቅሩ ከህ/ሰቡ ጋር በመናበብ በአጋቾች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድም ጠይቀዋል። እንደአብነት ሲጠቅሱም መስከረም 3 ቀን 2014 ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ አንድ የ13 ዓመት ህጻን ልጅ በጎንደር ከተማ ሽንታ በተባለው አካባቢ ታግቶ ስለመወሰዱ ገልፀዋል። የታገተው ህጻን ቤተሰቦችም 800 ሺህ ብር በአፋኞች ስለመጠየቃቸው የገለፁት ነዋሪዎች የሁኔታውን አሳሳቢነት ተረድተን በአስቸኳይ መፍትሄ መፈለጉ ይበጀናል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply