በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአሊያንስ ስታር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤት አቶ ምህረት አስረስ ህክምና ላይ ለሚገኙ የህልውና ዘማቾች 100 በጎችን በድጋፍ ሰጡ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአሊያንስ ስታር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤት አቶ ምህረት አስረስ ህክምና ላይ ለሚገኙ የህልውና ዘማቾች 100 በጎችን በድጋፍ ሰጡ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአሊያንስ ስታር ስራ አስኪያጅ አቶ ደሴ ምስጋናው እንደገለፁት የአሊያንስ ስታር ኃላፊነቱ የግል ኩባንያ ከአሁን ቀደም 2 ነጥብ 2 ሚሊን ብር ግምት ያለው ብስኩት በሁመራ ግንባር ድጋፍ አድርጓል፡፡ 485ሽህ ብር ግምት ያላቸው 20 በሬዎችን በማይጠምሬ ግንባር ለሚገኙ የህልውና ዘማቾች ድጋፍ ማድረጉንም ገልፀዋል፡፡ በጎንደር ከተማ ለህልውና ዘመቻ ገቢ ማሰባሰቢያ በተከፈተ የሒሳብ ቁጥር 5መቶ ሽ ብር በአማራ ክልል የህልውና ዘመቻ ገቢ ማሰባሰቢያ በተከፈተ የሒሳብ ቁጥር 3 ሚሊየን ብር ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ማድረጉን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡ በዛሬው ዕለትም 500ሽ ብር ግምት ያላቸውን 100 በጎችን ህክምና ላይ ለሚገኙ የህልውና ዘማቾች ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ የአሊያንስ ስታር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ እስካሁን ለህልውና ዘመቻው ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የጥሬ ገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል። የበጎች ርክክብ ስነ-ስርዓት ጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የህልውና ዘመቻ የሀብት አሰባሳቢ ኮሜቴ ሰብሳቢ አቶ ተሾመ አግማስና የጎንድር ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክትር አሽናፊ ታዘበው በተገኙበት ተከናውኗል፡፡ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአስተዳደርና ቢዝነስ ዳይሮክትሬት ዳይሬክተር አቶ ዓለም አቀፍ ዋኛው መለሰ እንደገለፁት የአሊያንስ ስታር ባለቤት አቶ ምህረት አስረስ ህክምና ላይ ለሚገኙ የህልውና ዘማቾች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ህብረተሰቡ በህግ መስከበረም ሆነ በህለውና ዘመቸው ለህዝብ ብለው በህክምና ላይ ለሚገኙ ዘማቾች እያደረገ ያለውን ድጋፍ የሚበረታታ ነው፡፡ ይህን አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል። በተያያዘ በህልውና ዘመቻው ለተሰው ዘማች ቤተሰቦች የዘመን መለወጫ በዓልን ምክኒያት በማድረግ የበግ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። በትምህርት ገበታ ላይ ለሚገኙ የዘማች ቤተሰቦችም መንግስት ነፃ የትምህርትና የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተገልጧል፡፡ በጎንደር ከተማ አስተዳደር በማራኪ ክፍለ ከተማ በህልውና ዘመቻው ለተሰው ታጋይ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው ለዘምን መለወጫ በዓል የሚውል የበግ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ እንደገለፁት በዘመቻው የተሰውት ወንድሞቻችን ለሀገር ክብርና ለህዝቦች ደህንነት ሲሉ ህይወታቸውን የሰጡ ጀግኖች ናቸው፡፡ እነዚህ ጀግኖች ወንደሞቻችን ስማቸው ከምደር በላይ ሲወሳ ይኖራል፡ሲሉ ከንቲባው ገልፀዋል፤ እነዚህ ታጋች ለዓለማቸው ሲሉ ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ናቸው፤ ለእነዚህ ወንድሞቻችን መንግስት ከፍ ያለ ክብር አለው ብለዋል ሲል የጎንደር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply