በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ // አሻራ ሚዲያ  ህዳር፡-22/03/13/ዓ.ም //… በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም…

በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ // አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-22/03/13/ዓ.ም //… በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም…

በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ // አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-22/03/13/ዓ.ም //… በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጻል። የከተማው ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ የከተማው ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል። ግለሰቡ ለሽብር ተግባር ለመጠቀም ካዘጋጃቸው 35 ተቀጣጣይ ቁሳቁስ፣ 216 ማሰልጠኛ ማንዋል፣ ሶስት የተለያዩ ባንኮች ደብተር፣ 20 ገንዘብ ገቢና ወጪ ደረሰኝ እና ከአንድ ላፕቶፕ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ተናግረዋል፡፡ በግለሰቡና በግብረ አበሮቹ ላይ የሚደረገው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር አየልኝ ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጥም ጠቅሰዋል። በመጨረሻም ህብረተሰቡ ጥንቃቄና ክትትል እንዳለበትና ተናግረዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply