You are currently viewing በጎንደር ከተማ የአብን ሰብሳቢ አባይ ረዳ ለውይይት እንፈልግሃለን ብለው በጠሩት መንግስታዊ የአፋኝ ቡድን አካላት በቁጥጥር ስር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ግንቦት 15 ቀን 2014…

በጎንደር ከተማ የአብን ሰብሳቢ አባይ ረዳ ለውይይት እንፈልግሃለን ብለው በጠሩት መንግስታዊ የአፋኝ ቡድን አካላት በቁጥጥር ስር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 15 ቀን 2014…

በጎንደር ከተማ የአብን ሰብሳቢ አባይ ረዳ ለውይይት እንፈልግሃለን ብለው በጠሩት መንግስታዊ የአፋኝ ቡድን አካላት በቁጥጥር ስር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር ከተማ የአብን ሰብሳቢ አባይ ረዳ ለውይይት እንፈልግሃለን ብለው በጠሩት መንግስታዊ የአፋኝ ቡድን አካላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል። ግንቦት 15/2014 ረፋድ ላይ ወደ በማራኪ ክ/ከተማ ከሚኖርበት በቀጥታ በእጅ ስልኩ የደወሉ መንግስታዊ የአፋኝ ግብረ ኃይል አባላት “አንዳንድ ነገሮችን እንድናወራ ቢሮህ ድረስ መጥተን ነበር” እንዳሉት ለማወቅ ተችሏል። እንፈልግሃለን ብለው ስለደወሉለትም ሄዶ አግኝቷቸዋል፤ እንዳገኛቸውም አፍነው ወደ ማራኪ ክ/ከተማ 3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ አስረውታል። ግንቦት 14/2014 ከተገላገለችው ባለቤቱ ነጥለው ወስደው አስረውታል። በአፈና ላይ የተሰማራው ግብረ ኃይል በጎንደር እና አካባቢው እስር፣ወከባ እና ሽብር እየፈጠረ በመሆኑ በርካታ የሚሆኑ የጎንደር እና የአካባቢው ወጣቶች እና የፋኖ አባላት ወደ ኤርትራ ሲሻገሩ፣ ከፊሎች ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለመሰደድ ተገደዋል። የምኒልክ ብርጌድ ዋና አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ፣ ምክትሉ አርበኛ መብራቱ አረጋ እና አባላቱ ወደ ወልቃይት እንዳይሄዱ ከመከልከላቸው በላይ ሻለቃ አንተነህ ድረስ መታሰሩ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም አመራር እና አባላትን እያሳሰርን ከጠላት የማረክነውን ብሬን አሳልፈን አንሰጥም በማለት ከአምስት ዓመታት በላይ በርሃ በትግል ላይ የቆዩት እነ አርበኛ መብራቱ አረጋ ወደ ጫካ መግባታቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply