በጎንደር ከተማ 10ኛው የባህል ፌስቲቫልና 3ተኛው የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ ደጋፊዎች ሩጫ ተካሄደ

በጎንደር ከተማ 10ኛው የባህል ፌስቲቫልና 3ተኛው የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ ደጋፊዎች ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጎንደር ከተማ 10ኛው የባህል ፌስቲቫልና 3ተኛው የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ ደጋፊዎች ሩጫ ዛሬ ተካሄደ።
በባህል ፌስቲቫሉ ላይ የጎንደር ከተማ ባህላዊ ትውፊቶችና እሴቶች በተለያዩ የከተማዋ የኪነ ጥበብና ባህል ቡድኖች ቀርበዋል።
የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ ደጋፊዎችም 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ያካሄዱ ሲሆን÷ መነሻውን ፕላዛ 18 አድርጎ ፒያሣ ላይ ተጠናቋል።
ዛሬ የተካሄዱት መርሓ ግብሮች ለጥምቀት መዳረሻ በከተማዋ ላይ ሲካሄዱ የነበሩ ዝግጅቶች ማጠናቀቂያ ናቸው።
በከተማዎ ከጥር አምስት ጀምሮ በየእለቱ የጥምቀት መዳረሻን መነሻ ያደረጉ የተለያዩ መርሓ ግብሮች ሲከናወኑ ቆይተዋል።
በዓሉን ለማክበርም ከተለያዩ የሀገሪቱ የዓለም ክፍሎች የመጡ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እየገቡ ይገኛሉ።
በዘቢብ ተክላይ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በጎንደር ከተማ 10ኛው የባህል ፌስቲቫልና 3ተኛው የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ ደጋፊዎች ሩጫ ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply