You are currently viewing በጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራ እና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ ወሰን ሰላምና ልማት አስመላሽ ኮሚቴ ለፌደሬሽን ም/ቤት ደብዳቤ ማስገባቱን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

በጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራ እና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ ወሰን ሰላምና ልማት አስመላሽ ኮሚቴ ለፌደሬሽን ም/ቤት ደብዳቤ ማስገባቱን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

በጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራ እና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ ወሰን ሰላምና ልማት አስመላሽ ኮሚቴ ለፌደሬሽን ም/ቤት ደብዳቤ ማስገባቱን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራ እና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ ወሰን ሰላምና ልማት አስመላሽ ኮሚቴ ነሃሴ 10/2014 ለፌደሬሽን ም/ቤት ደብዳቤ ማስገባቱን እና ተቋሙም ደብዳቤያቸውን የተቀበለ መሆኑንና ስለማረጋገጡ ያስታወቁት የኮሚቴው ሰብሳቢ መምህር ጸጋዬ እሸቴ ናቸው። በጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራ እና ሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ ወሰን፣ ሠላምና ልማት አስመላሽ ኮሚቴ ሰምንት የሚሆኑ አመራሮችና አባላቱን በመወከል ወደ አዲስ አበባ መላኩ ተገልጧል። ለፌደራል መንግስትና ለተለያዩ የሚዲያ እና የሰብአዊ መብት ተቋማት የጠለምት አማራ ማንነት እና ወሰን ጥያቄ በአጭር ጊዜ እንዲታይ የመጠየቅ ተልዕኮን ይዘው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው ታውቋል። የጠለምት አማራ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ በሰሜን አውራጃ ስር በአድርቃይ እና በጠለምት ወረዳ አስተዳደር ስር ስንተዳደር የነበረ ቢሆንም በሰሜን እና በምስራቅ የተከዜ ወንዝ በምዕራብ የወልቃይት ጠገዴና ሁመራ ወረዳዎች የሚዋሰን ሆኖ በጥንቱ ሰሜንና በጌምድር ጠቅላይ ግዛት ስር ቀጥሎም በጎንደር ክፍለ ሀገር በኋላም በሰሜን ጎንደር ክፍለ ሀገር በሰሜን አውራጃ ስር በጎንደር አስተዳደር ክልል ውስጥ የነበረ ስለመሆኑ አውስቷል። ከህዝቡ ፍላጎት ውጭ የማናውቀው የትግሬ ማንነት በሀይል ተጭኖብን ከአድርቃይ ወረዳ እና ከጠለምት ወረዳ ተቆርሶ ወደ ትግራይ የተወሰደ ህዝብ ስለመሆኑ በደብዳቤው ተመላክቷል፡፡ በተለይም ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ፈቃዱን ሳይጠየቅ ወደ ትግራይ ክልል መካተቱን በመቃወም የሚኖር ሲሆን ለ30 ዓመታት ታሪክ አዋቂዎች እና ተቃውሞ የሚያቀርቡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአካባቢው ተወላጆች አብዛኛዎቹ በትህነግ ታጣቂዎች በሌሊት እየታፈኑ የደረሱበት የማይታወቅ ሲሆን ከፊሎቹ ምክንያት እየተፈጠረ በራሳችን ምድር ፍየል ውሃ በተባለው ቦታ ከፍተኛ ስቃይ በሚፈጸምበት የጉድጓድ እስር ቤት እንደሚሰቃዩ ተገልጧል። ከፍተኛ ግፍና በደል እየተፈፀመባቸውም ጥያቄ ከማቅረብ ያላቆረጡ ቢሆንም ሰሚ በማጣታቸው አሁንም ድረስ ወደ ትግራይ የተወሰደው የጠለምት ህዝብ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ይገኛል ብሏል፡፡ የኮሚቴ አመራር እና አባላት ቤተሰቦች እና ማንኛውም የማንነት ጥያቄ ያነሳል ተብሎ በትህነግ የተጠረጠረ ሁሉ አካባቢውን ለቆ እንዲሰደድ በመደረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችን ደግሞ ወደ ጠለምት እየመጡ እንዲሰፍሩ በመደረጉ ግልጽ የሆነ የዲሞክራፊ ለውጥ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል። በሰሜን ጎንደር ዞን አምስት የጠለምት ወረዳዎች አሁን ላይም በአሸባሪው እና ወራሪው ትሕነግ አፈና ስር እንደሚገኙ ይታወቃል። በብሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች በደባርቅ፣በዳባትና አካባቢው ያለ በቂ መጠለያ እና ሰብአዊ ድጋፍ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ኮሚቴው በአጠቃላይ የአማራ ማንነትና የወሰን ጥያቄው በአስቸኳይ እንዲመለስለት፣ የዘመናት ግፍ እና ጭቆና ቀርቶ በአፈና ስር ያለው የጠለምት አማራ ህዝብ ነጻ እንዲወጣ እየጠየቀ ይገኛል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply