You are currently viewing በጎጃም ጎንደር መስመር ያቀናው የባልደራስ ቡድን የድጋፍ መስጠት  ተልዕኮውን በስኬት አጠናቆ ተመለሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል  ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም       አዲስ አበባ ሸዋ በጎጃም…

በጎጃም ጎንደር መስመር ያቀናው የባልደራስ ቡድን የድጋፍ መስጠት ተልዕኮውን በስኬት አጠናቆ ተመለሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎጃም…

በጎጃም ጎንደር መስመር ያቀናው የባልደራስ ቡድን የድጋፍ መስጠት ተልዕኮውን በስኬት አጠናቆ ተመለሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎጃም ጎንደር መስመር ያቀናው የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድጋፍ አስተባባሪ ቡድን ከትህነግ የጥፋት ኋይል ጋር ግንባር ለግንባር እየተፉለሙ መስዋእትነት በመክፈል ላይ ለሚገኙ፣ ለአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) እና ለመከላከያ ሰራዊቱ፣ እንዲሁም በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የቁሳቁስ እና የአልሚ ምግቦች ድጋፍ አድርጓል። የሰብአዊ እርዳታዉን በጭና አካባቢ በወራሪው የትህነግ ሃይል ጉዳት ለደረሰባቸው ንፁሃን ወገኖቻችን ያደረሰ ሲሆን፣ ድጋፋ ለህጻናት የሚሆን የአልሚ ምግብ፣ ኢንዶሚን፣ ፓስታ፣ዘይት፣ዱቄት እና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያን ያካተተ ነዉ። ለህዝባዊ ኃይሉ (ፋኖ) እና መከላከያ ሰራዊት የሚዉለዉን የደረቅ ምግቦች ኮቸሮ፣ዘይት፣ምስር እንዲሁም ሸበጥ፣ሽርጥና ከስክስ የመሳሰሉትን የድጋፍ አይነቶችን ለታጋይ ንግስት ይርጋ በጎንደር ከተማ በመገኘት አስረክቧል። በጎጃም ጎንደር ግንባር ያቀናው የባልደራስ የእርዳታ አስተባባሪ ቡድን በተለያዩ ቦታዎች ያደረሰዉን ድጋፍ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ መሆኑ ተገልጧል። ባልደራስ በሰሜኑ ጦርነት ከትህነግ የጥፋት ኃይል ጋር ግንባር ለግንባር እየተፉለሙ መስዋእትነት ጭምር በመክፈል ላይ ለሚገኙ ህዝባዊ ኃይሎች በተለይም ፋኖ እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ንፁሃን ዜጎቻችን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል ባልደራስ። በጎጃም ጎንደር መስመር የተጓዘው የድጋፍ አስተባባሪው ታህሳስ 21 ቀን 2014 በባሕር ዳር ከተማ በመገኘት ለአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በጦር ሜዳ ለከፈለው እና እያደረገ ለሚገኘዉ ተጋድሎ የቁሳቁስ እና የሞራል ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል። በተመሳሳይ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን እና ከአሸባሪው ኃይል ጋር ፊት ለፊት እየተፋለሙ ላሉት የወገን ጦር አባላት ድጋፍ ለማድረግ ከአዲስ አበባ – ደብረ ብርሃን – ሸዋ ሮቢት- ኮምቦልቻ- ደሴ-ኩታ በር ፤ የተሰማራው ግብረ ኃይል የተሳካ ሥራ ማከናወኑ ይታወቃል። በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ በክብር መሰዋት የሆኑት የአቶ እሸቴ ሞገስ እና የልጃቸውን የይታገስ እሸቴ ቤተሰብን ቤት በመጎብኘት የሐዘናቸው ተካፋይ በመሆን ማጽናናታቸውና ለሸዋሮቢት ፋኖዎች ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል። ፓርቲው በሰሜን ወሎ ከተማ ወልድያ በመሄድ ፣ ለወልደያ ህዝብ ሙስሊም ክርስቲያን ሳይመርጡ ለ516 አስከፊ ቀናት ህብረተሰቡን ሲያጽናኑ ፣እየለመኑ ሲመግቡ ከነበሩት ከብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ጋር በመገናኘት ለተጎጅዎች ድጋፍ ማድረጉ ተዘግቧል። በአፋር የተሰማራው ድጋፍ ሰጪ ግብረኃይል ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ መፈጸሙንና ከአፋር ክልል ፕሬዚደንት ሃጂ አወል አርባ ምስጋና የቀረበለት መሆኑ አይዘነጋም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply