በጎጃም ጎንደር መስመር ያቀናው የባልደራስ ቡድን የድጋፍ መስጠት ተልዕኮውን በስኬት አጠናቆ መመለሱን አስታወቀ። ታህሳስ 24/ 2014/አሻራሚዲያ/ በጎጃም ጎንደር መስመር ያቀናው የባልደራስ…

በጎጃም ጎንደር መስመር ያቀናው የባልደራስ ቡድን የድጋፍ መስጠት ተልዕኮውን በስኬት አጠናቆ መመለሱን አስታወቀ። ታህሳስ 24/ 2014/አሻራሚዲያ/ በጎጃም ጎንደር መስመር ያቀናው የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድጋፍ አስተባባሪ ቡድን ከትህነግ የጥፋት ኋይል ጋር ግንባር ለግንባር እየተፉለሙ መስዋእትነት በመክፈል ላይ ለሚገኙ፣ ለአማራ ህዝባዊ ሃይል(ፋኖ) እና ለመከላከያ ሰራዊቱ፣ እንዲሁም በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የቁሳቁስ እና የአልሚ ምግቦች ድጋፍ አድርጓል ብሏል በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀው ። የሰብአዊ እርዳታዉን በጭና አካባቢ በወራሪው የትህነግ ሃይል ጉዳት ለደረሰባቸው ንፁሃን ወገኖቻችን ያደረሰ ሲሆን፣ ድጋፋ ለህጻናት የሚሆን የአልሚ ምግብ፣ ኢንዶሚን፣ ፓስታ፣ዘይት፣ዱቄት እና የሴቶች ንጽህና መ…ጠበቂያን ያካተተ ነዉ ያለ ሲሆን። ለህዝባዊ ኋይሉ ፋኖና መከላከያ ሰራዊት የሚዉለዉን የደረቅ ምግቦች ኮቸሮ፣ዘይት፣ምስር እንዲሁም ሸበጥ፣ሽርጥና ከስክስ የመሳሰሉተን የድጋፍ አይነቶችን ለለታጋይ ንግስት ይርጋ በጎንደር ከተማ በመገኘት አስረክቧል ብሏል። በጎጃም ጎንደር ግንባር ያቀናው የባልደራስ የእርዳታ አስተባባሪ ቡድን በተለያዩ ቦታዎች ያደረሰዉን ድጋፍ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ለይ ይገኛል። ባልደራስ በሰሜኑ ጦርነት ከትህነግ የጥፋት ኋይል ጋር ግንባር ለግንባር እየተፉለሙ መስዋእትነት ጭምር በመክፈል ላይ ለሚገኙ ህዝባዊ ኋይሎች በተለይም ፉኖ እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ንፁሃን ዜጎቻችን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል አስታውቋል ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply