You are currently viewing በጎ ፈቃደኛ የሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ከወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ አስኮ እና ካራ ቆሬ አካባቢ ለሚገኙ አማራዎች ከጎናቸው በመሆን እንደሚደግፏቸ…

በጎ ፈቃደኛ የሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ከወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ አስኮ እና ካራ ቆሬ አካባቢ ለሚገኙ አማራዎች ከጎናቸው በመሆን እንደሚደግፏቸ…

በጎ ፈቃደኛ የሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ከወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ አስኮ እና ካራ ቆሬ አካባቢ ለሚገኙ አማራዎች ከጎናቸው በመሆን እንደሚደግፏቸው ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎ ፈቃደኛ የሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በማህበራዊ ሚዲያ ትስስር በመፍጠር በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ከወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ የመጡ አማራዎችን በአስተባባሪያቸው በኩል ጠይቀዋል። በወለጋ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ጭምር የደረሰባቸውን ግፍ ተመልክተዋል። የበጎ ተግባር አስተባባሪው የአየር መንገድ ሰራተኛ ጀንበሩ ገንብር እንዳለው ከወለጋ ተፈናቅለው በብዙ መከራ አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 15 አስኮ ከተጠለሉበት የወጣቶች ማዕከል እንዲወጡ እና ሜዳ ላይ እንዲጣሉ መደረጉ አሳዛኝ እንደነበር አውስቷል። በሌላ በኩል በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ተቆርቋሪ ወገኖች ባደረጉት ድጋፍ ቤት ለመከራየት መብቃታቸው መልካም ስሜት የፈጠረለት መሆኑን ተናግሯል። ሌላው በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ዘነበ ወርቅ በአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃይ አማራዎች በፖሊስ አባላት ጫና ከመጣችሁበት አካባቢ መጠለያ ተዘጋጅቷል በሚል ሽፋን ህዳር 13 ቀን 2014 ከተወሰዱ በኋላ የመበተናቸውን ዜና መስማት ብዙዎችን አሳዝኗል። በምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ አርጆ ጉደቱ ከተማ ለጊዜው ከተጠለሉበት የመከላከያ ካምፕ በኃላፊነት መጥቶ የሚያናግራቸውና የሰብአዊ እርዳታ የሚሰጣቸው በመጥፋቱ ምክንያት ሁሉም ተበታትነዋል፤ ቁጥራቸውም 120 ነበሩ። ከተበተኑት መካከል ቢያንስ ከ40 በላይ የሚሆኑት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው በመምጣት በተለያዩ በጎ ፈቃደኛ ሰዎች በረንዳ እና በዘመድ ቤት በመጠለል ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ገልጸዋል። በመንግስት አካላት በሚደገፈው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በእኩይ አላማ አስፈጻዎቹ ለዘመናት ከሚኖሩበት ቀያቸው በጦር መሳሪያ ጭምር በመታገዝ ከተፈጸመባቸው ጥቃት በሌሊት ሸሽተው ነፍሳቸውን ያተረፉ ናቸው። በጎ ፈቃደኛ የአየር መንገድ ሰራተኞችንና ጓደኞቹን በማስተባበር 22,600 ብር ይዞ የመጣው ጀንበሩ ገንብር ድጋሜ በኃይል ወደ ወለጋ እንዳይወሰዱ እየተጨነቁም ቢሆን ለአጭር ጊዜ ካራ ቆሬ ቅዱስ ገብርኤል ኮንዶሚኒዬም ሰፈር ተሰብስበው ለተገኙ ከ40 በላይ ለሚሆኑ አማራዎች 12,600 ብር፣ በአስኮ አንድ ግቢ ተከራይተው ለሚገኙት ደግሞ 10 ሽህ ብር በማከፋፈል በድምሩ ለጊዜው የ22,600 ብር ድጋፍ አስረክቧል። ተፈናቃይ አማራዎችም መንግስት የት ወደቃችሁ ብሎ በመጠየቅ አስቸኳይ የሆነ ሰብአዊ እርዳታ እና መጠለያ እንዲሰጣቸው ጥሪ አድርገዋል። ድጋፍ ያደረጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ተቆርቋሪዎች ከጎናቸው ስለሆኑ ያመሰገኑት ተፈናቃዮቹ ሌሎችም ወገናዊ ትብብር እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply