
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተፈጽመው የሚሰሙ ጠለፋዎች በአገር ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብነት እና በጋብቻ እንደሚጠናቀቁ ይሰማል። ይህ ደግሞ ጠላፊዎች በባሕላቸው ውስጥ በመሸሸግ ከሕግ ተጠያቂነት እንዲያመልጡ እያደረጋቸው ነው። በተጨማሪም የተጠቂዎቹን አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት የከፋ ያደርገዋል። የሕግ ባለሙያዎች የተጎጂዎች በደል በአግባቡ በፍትህ ሥርዓቱ መታየት እና በዳዮችም ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለባቸው ሲሉ ይናገራሉ።
Source: Link to the Post