በጠገዴ ወረዳ የሶሮቃ ከተማን የንፁህ መጠጥ ውሀ ችግር ይፈታል ተብሎ በ2007 ዓ.ም የተቆፈረውና የግንባታ ስራ የተጀመረለት ጥልቅ የጉድጓዱ ውሀ ፕሮጀክት እስካሁን አገልግሎት መስጠት አለመቻ…

በጠገዴ ወረዳ የሶሮቃ ከተማን የንፁህ መጠጥ ውሀ ችግር ይፈታል ተብሎ በ2007 ዓ.ም የተቆፈረውና የግንባታ ስራ የተጀመረለት ጥልቅ የጉድጓዱ ውሀ ፕሮጀክት እስካሁን አገልግሎት መስጠት አለመቻሉ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጠገዴ ወረዳ የሶሮቃ ከተማን የንፁህ መጠጥ ውሀ ችግር ይፈታል ተብሎ በ2007 ዓ.ም ጥልቅ ጉድጓዱ ከተቆፈረ በኃላ በ2011ዓ.ም ከዋናው የዉሀ መገኛ ወደ ማጠራቂሚያ ጋኑ ለማድረስ የውሀውን የግፊት መስመር ለአንድ ዋሽ የዉሀ ፕሮጀክት ሁለተኛውን ምዕራፍ በተሰጠው ዉል መሰረት ተገንብቷል። በመቀጠልም ምንም እንኳ ጊዚያዊ ርክክብ ቢደረግም ከዋናው የማጠራቀሚያ ጋን ወደ ከተማው የሚወስደውን የማሰራጫ መስመር ግንባታ ለመስራት ውል የወሰደው ተቋራጭ በዉሉ መሰረት ሰርቶ በወቅቱ ባለማስረከቡና አንዳንድ የጎደሉ ስራዎችን ማስተካከል አለመቻሉ ተገልጧል። በመሆኑም እስካሁን ድረስ የዉሀ ፕሮጀክቱ ለከተማው ማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት አልቻለም ሲሉ የጠገዴ ወረዳ ውሀ እና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ አዳነ አያሌው አስታውቀዋል። ውሀ የሰው ልጆች በህይወት ለመኖር ከሚያስፈልጓቸው መሰረታዊ ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛዉ በመሆኑ በተለይ በበርሀማው አካባቢ ካለው ከፍተኛ የሆነ የውሀ ፍጆታ አኳያ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ሲባል ይህ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ የሆነበት ፕሮጀክት ችግሮቹ ተፈተው በአጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት መስጠት ይችል ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት ትልቅ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ሲል ነው የጠገዴ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply