በጣሊያን ባለሀብቶች የተገነባው “ኢታካ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ” ወደ ውጭ ኤክስፐርት ማድረግ ጀመረ፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኘው ግዙፉ የኢታካ ኢንዱስትሪ ማምረትና ወደ ውጭ ኤክስፐርት ማድረግ መጀመሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህ ግዙፍ ኢንዱስትሪ በአለም ከ6ሺህ በላይ የመሸጫ ሱቆች ያሉት ትልቅ ኢንዱስትሪ ነው ተብሏል።

በሀገራችን በተለያዩ ክፍሎች በነበረው የሰላምና ፀጥታ ችግር ምክንያት ተዘግተውና ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ 390 ኢንዱስትሪዎች በራሳቸው ጥረትና በመንግሥት ድጋፍ ወደ ማምረት እንዲገቡ መደረጉንም ሰምተናል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አቶ ታረቀኝ ቡሉቶ በዚህ ሰዓት ትልቁ ችግራችን ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣የስራ ማስኬጃ የብድር አቅርቦት ፣ለካፒታል ፕሮጀክት የሚቀርበው ፋይናስ፣ከግብርና ጋር ተያይዞ የግብዓት የኋልዮሽ ትስስር ፣የውጭ የገበያ ትስስር አማራጭ ከመፍጠር ጋር ተያይዞና ሌሎችም ብዙ ልየታ የተደረጉ እንዳሉ ለጣቢያችን ገልፀዋል ።

አቶ ታረቀኝ ቡሉቶ መንግስት ባለፉት ስድስት ወራት በአምራች ኢንዱስትሪዎች መካከል ያሉት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ተግዳሮት ለመፍታ ጥረት አድርጓልም ነው ያሉት።

ቢሆንም ግን እንደ ሀገር የምናገኘው የውጭ ምንዛሬ የሚታወቅና በቂ ባለመሆኑ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ላይ አምራች ኢንዱስትሪው እንዲ ጠናከር የውጭ ምንዛሬ የሚያገኝበትንም መንገድ እንዲፈጥር አሁንም ለአምራች ኢንዱስትሪው ቅድሚያ ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል።

በልዑል ወልዴ

መጋቢት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply