በጤናው ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ባለሙያዎች የዕውቅናና ሽልማት ተበረከተላቸው የጤና ሚኒስቴር 23ኛው ጉባኤን ምክንያት በማድረግ ለዘርፉ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጥቷል።በዚህም የህይዎት ዘ…

በጤናው ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ባለሙያዎች የዕውቅናና ሽልማት ተበረከተላቸው

የጤና ሚኒስቴር 23ኛው ጉባኤን ምክንያት በማድረግ ለዘርፉ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጥቷል።

በዚህም የህይዎት ዘመን ተሸላሚ በመሆን ሲስተር ፍሬዎት ደምሰው፣ከሀረር ፣ዶክተር ገረመው ጣሰው፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ዶክተር ሀዲስ ሰለሞን እንዲሁም አቶ ሙሳ ሰይድ ከሶማሌ ክልል ተሸላሚ ሆነዋል።

በሙያ መስክ የላቀ ሥራና አፈፃፀም በማበርከት ዶክተር አዱኛ ወይሳ፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ ዶክተር አታክልቲ ባራኪ ከአለርት ሆስፒታል ፣ አቶ በላይ በዛብህ፣ ከህብረተሰብ ጤና ተሸላሚ ሆነዋል።

በተለያዩ የሥራ ሃላፊዎች ተሸላሚ የሆኑት ደግሞ፣ዶክተር ጌታቸው አዲስ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ አቶ ቃሬ ጫዊቻ፣ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ፣ አቶ ነጋሽ ስሜ፣ ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ፣ ሽልማታቸውን ወስደዋል።

በልዩ ተሸላሚነት ደግሞ ዶክተር ማረልኝ አንተንብዬ ከሶማሌ ክልል ተሸላሚ ሆነዋል ።

አባቱ መረቀ
ጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply