በጤናው ዘርፍ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ሀገር አቀፍ የጤና አመራር ኘሮግራም መዘጋጀቱ ተነገረ።

ጤና ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ ዉጤታማ የጤና አመራር ኘሮግራም ማስታወቂያ እና ማስጀመሪያ መርሀግብር በዛሬዉ ዕለት አካሂዷል።

ባለፉት አመታት በሀገር ደረጃ የጤና ስርአቱን ዉጤታማ ለማድረግ የተሰሩ በርካታ ስራዎች ቢኖሩም በቂ እንዳልሆነ በመድረኩ ተነስቷል።

የጤና ስርአቱን በማዘመን አዲስ የአመራርና የጤናውን ሁኔታ ለማሻሻል፣ የአመራር ብቃቶችን ለማሳደግ ፣ ሀገራዊ እና ተቋማዊ አሻራዎችን ለማስቀመጥ አላማውን ያደረገ ነው ተብሏል።

የተለያዩ እቅዶች በስራ ላይ መዋላቸውን እና አመራርን ከማዘመን አንፃር ሴቶችን ያካተተ የአመራር አቅምን መፍጠርም ሌላኛው አላማው መሆኑን ሰምተናል።

ከተለያዮ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆንም የጤና ስርአቱን ለማሻሻል በርካታ ስራዎች መሰራታቸውም ተነስቷል።

በሀገሪቱ ያለውን ውስን ሀብት በመጠቀም ያለውን የጤና ስርአት ማሳደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነት ነውም ተብሏል።

በሐመረ ፍሬዉ

ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply