በጤና ተቋማት የኦክስጅን ፍንዳታ እንዳያጋጥም በቂ ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።

ኦክስጂን ለኮሮና ቫይረስ ታማሚ ከፍተኛ ድጋፍ እየሰጠ ቢሆንም ፍንዳታ ሲያጋጥም በሠዉ ህይወትና በጤና ተቋማት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም።በተለያዩ አለም ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ የኦክስጅን ፍንዳታ አጋጥሞ ዜጎች መሞታቸው ይታወሳል ።አሐዱም የጤና ሚኒሰቴር በኮቪድ ማገገሚያ ተቋማት ላይ የኦክስጅን ፍዳታ እንዳያጋጥም ምን ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ሲል ጠይቋል ።

የጤና ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ለአሐዱ እንደገለፁት በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከላት ፍንዳታ እንዳይከሰት ከሙሌት ጀምሮ ከፋተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ብለዋል።ኦክስጀን ከሚመረትበት ቦታ ስርጭት እንዲደረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ዶ/ር ደረጀ ገልፀው እስካሁን በሀገሪቱ ከኦክስጀን ጋር በተያያዘ የከፋ የሚባል ችግር እንዳላጋጠመ ተናግረዋል ።የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሲጨምር የኦክስጅን ተጠቃሚው ቁጥር እየጨመረ ስለሚሄድ ተያያዥ ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል ።

*****************************************************************

ቀን 30/04/2013

አሀዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply