በጥበቃ ስራ ላይ የውጭ ሀገር ዜጎች መሰማራታቸው በስራችን ላይ ክፍተኛ አደጋ ጥሎናል ሲል አባይ የጥበቃ አሰሪዎች ማህብር ቅሬታውን አሰማ፡፡በኢትዮጵያ የመኖርያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸው…

በጥበቃ ስራ ላይ የውጭ ሀገር ዜጎች መሰማራታቸው በስራችን ላይ ክፍተኛ አደጋ ጥሎናል ሲል አባይ የጥበቃ አሰሪዎች ማህብር ቅሬታውን አሰማ፡፡

በኢትዮጵያ የመኖርያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች በጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ የገለጸው ማህበሩ ዘርፉ ላይ የነበረውን ተግዳሮት ይበልጥ የሚያወሳስብ ነው ብሎታል፡፡

ማህበሩ እንዳለው በህግና ደንብ የማይመሩ ነዋሪነታቸውን የውጭ ሃገራትን ያደረጉ ተቋማት ወደሀገር ውሥጥ በመግባት የዘርፉን ታማኝነት አደጋ ላይ የሚጥል ስራ እየከወኑ እንደሚገኙ ባደረገው ማጠራት ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ከ31 በላይ አባላትን በስሩ አቅፎ የሚገኘው አባይ የጥበቃ አሰሪዎች ማህበር ከ21 ሺ በላይ ሰራኞችን ደግሞ በጥበቃ ስራዎች ላይ አሰማርቶ በማሰራት የዜግነት ግዴታውን በታማኝነት እየተወጣ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ላለፉት ስድስት ወራት ባደረገው ማጣራት ህግ እና ደንብ የማይፈቅድላቸው የውጭ ዜጎች ቢሮ ተከራይተው በህገ-ወጥ መንገድ በማገኛኘት በህግ የተከለከለውን ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ብሏል፡፡
የጥበቃን ስራ ለመስራት ኢትዮጵያዊ መሆን ይገባቸወዋል የሚልውን አዋጅ በሚጻረር መልኩ ከው-ውጭ ሀበገር የገቡ ዜጎች መኖራቸውን የገለጸው ማህሩ መንግስት ይህ ችግር ሊቀረፍ እንደሚገባው የህግ ጠበቃ ማሪያ ካሳዬ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አዋጅ 1180/20 እሱን ተከትሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 474/20 አንቀጽ ንኡስ ቁጥር 29 የጥበቃ ስራ ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የተፈቀደ መሆኑን ይደነግጋል ነገር ግን ይህንን በሚጸረር መልኩ ሶስተ/3/ ደርጅቶች ወደ ስራ መግባታቸውን የአባይ የጥበቃ አሰሪዎች ማህብር ባደረገው ማጣራ እንዳረጋገጠ አስታውቋል፡፡

በአዋጁ መሰረት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው የውጭ ሀገር ዜጋ በጥበቃ ስራ ላይ መሰማራት እንደማይችል ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በቀድሞው አዋጅ ቁጥር 632/2001 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ ወይም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና ይህን መመሪያ በመተላለፍ የሰራተኞችን መብትና ደህንነት በመጣሱ ምክንያት የተሰረዘ ኤጀንሲ ህገ-ወጥ እንደሆነ ተቆጥሮ ፍቃድ እንማያገኝ ይገልጻል ይሁን እንጅ ከአዋጅ እና ደንብ ወጭ ህገ-ወጥ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ማህበሩ እንዳለው ደንብን ሳይጠብቁ በውጭ ሀገራት ዜጎች ተከፍተው በአዲስ አበባ ህግ መብት ያልሰጣቸው PRS፣CGT እና AMARANTE የተባሉ የወጭ ሀገር ዜጎች የሚስተዳድሯቸው ድርጅቶች ህግና ደንብ የማይፈቅደውን ስራ በመስራት በማህበችን አባላት ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረሱ ነውም በማለት ተናግረዋል፡፡

ማህበሩ አጣራሁት ባለው መረጃ እነዚህ ድርጅቶች ህጋዊ በህግ እና ደንብ ስራ እንዳይሰሩ ቢከለክላቸውም እነሱ ግን ጥበቃዎችን አሰማርተው ወደ ስራ መግባታቸውን ማህበሩ አረጋግጧል፡፡
ከፍተኛ ጥንቃቄ በሚጠይቀው ስራና ሙያ የሃገሪቱን ህግና ደንብ ወደ ጎን ብለው በገቡ ተቋማት ምክንያት ስራቸውን አክብረው በሚሰሩ የማህበሩ አባላት ላይ ጫና እንዳሳደረ ነው ሲል ማህበሩ መንግስት ይወቅልኝ ብሏል፡፡

በመሆኑም ችግሩ እየተባባሰ ሳይመጣ መንግስት በነዚህ ድርጅቶች ላይ አስፈላገውን ማጣራት አድርጎ የመፍትሄ እርምጃ በመውሰድ በዘርፉ ላይ ያንዣበበውን አደጋ እንዲታደግ ማህበሩ አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply