በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው መካነ ሰላም ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ….

በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው መካነ ሰላም ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት በአሸባሪው ትሕነግ እና በኦነግ ሸኔ ግልጽ ጦርነትና ወረራ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው 400 ለሚሆኑ አባውራዎች፣ አረጋውያን፣ ነፍሰጡር፣ እመጫት፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኛ ለሆኑ እና ቋሚ በሽታ ላለባቸው ወገኖች ነው በመካነ ሰላም ከተማ ተገኝቶ ድጋፍ ያደረገው። ተጎጅዎቹ በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም እንዲሁም በቅርብ ቀን ደግሞ ከወለጋ በግፍ ተፈናቅለው በከተማው የሚገኙ ናቸው። በዚህም ብር 700,000 ብር /ሰባት መቶ ሺ ብር / ወጭ በማድረግ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ የንጽህና መጠበቂያዎች፣ የህጻናት ምግቦችና የወጥ እህሎች በድርጅቱ ተበርክቶላቸዋል። ይሄ ስራ እንዲሳካ የተባበሩ ማህበሩን በገንዘብ የደገፉ በሲዊድን እና በዋሽንግተን ሲያትል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ተመስግነዋል። የደቡብ ወሎ ምግብ ዋስትና ሀላፊ አቶ መሳይ ደግሞ ቀና ትብብር ማድረጋቸውን የገለጸው ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት ኃላፊውን ከልብ ማመስገኑን ገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply