በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወደ ቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው

በጦርነቱ ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የመጡ የወሎና የአካባቢው ኗሪዎችን ወደ መኖሪያ ቦታቸው የመመመለስ ሥራ እየተካሄደ ነው፡፡

አዲስ አበባ የሚገኘው የልዩ አውቶቡስ ትራንስፖርት ማኅበራትና ድርጅቶች የጋራ ኮሚቴ ተፈናቃዮቹን በነጻ ወደ አካባቢያቸው የመመለስ ሥራ ዛሬ የጀመረ ሲሆን አገልግሎቱ ለተከታታይ አራት ቀናት ይቀጥላል ተብሏል፡፡

በደብረ ብርሃንና በባህርዳር በተመሳሳይ ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖችን ወደ አካባቢያቸው እንዲገቡ የወሎ ህብረት የልማትና የበጎ አድራጎት ማኅበር ጥሪ አቅርቧል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply