በጦርነት ለተጎዱና በጦርነት ከበባ ውስጥ ላሉ ወገኖች መንግስት ፣ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ተቋማት የሰብአዊ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ግፊት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቆመ። አሻ…

በጦርነት ለተጎዱና በጦርነት ከበባ ውስጥ ላሉ ወገኖች መንግስት ፣ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ተቋማት የሰብአዊ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ግፊት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቆመ። አሻራ ሚዲያ መስከረም 5 ቀን 2014 ዓ.ም ባህርዳር_ኢትዮጵያ በሰሜን ወሎ ዞን፣ በደቡብ ወሎ ወረባቦ፣ በዋግ ኽምራ ሰቆጣና አካባቢው፣ በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ፣ በምዕራብ ጎንደር መተማ ሽንፋ፣ በሰሜን ጎንደር አዳርቃይና ማይጠብሪ እንዲሁም በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት፣ ክምር ድንጋይ እና አካባቢው በአሸባሪው ትሕነግ ግልፅ ወረራና ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ንፁሃን አማራዎች በግፍ መጨፍጨፋቸውና በመቶ ሽህዎች መፈናቀላቸው ይታወቃል። በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በሆሮ ጉድሩ ዞኖች በአማራዎች ላይ ያነጣጠረውን ማንነት ተኮር ጥቃት በአሸባሪው ኦነግ ሸኔና በተባባሪዎቹ ተጠናክሮ መቀጠሉም አይዘነጋም። በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማሼ ዞን እንዲሁም በመተከል ዞኖች የጉምዝ ታጣቂዎች በአማራዎች ላይ በየጊዜው የጅምላ ፍጅት እየፈፀሙ ይገኛሉ። ይህን ተከትሎም በሶስቱ የኦሮሚያ ዞኖች፣ በመተከል እና በከማሼ ዞኖች የሚኖረው የአማራ ህዝብ ከጥቃቱ ባሻገር አሁን ላይም ተፈናቅሎ ወደ ከተሞች አካባቢ ተሰባስቦ ባለበት በከባድ የጦርነት ከበባ ውስጥ እንደሚገኝ ግልፅ ነው። ስለችግሩ አስከፊነት የሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቃይ እንደገለፁት ለተጎዱና በጦርነት ከበባ ውስጥ ላሉ ወገኖቻችን አስቸኳይ የሰብአዊ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ ያስፈልገናል ያሉ ሲሆን ለተጎጅ ወገኖቻችን መንግስት ፣ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ተቋማት አስፈላጊውን የሰብአዊ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ ግፊት ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ በመንግስት የቅድመ ዝግጅት ጉድለትና ተፈፅሟል አሻጥርም ጭምር የሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው፣ ጽንፈኛው፣ ተስፋፊውና ወራሪው የትሕነግ ቡድን መያዙን ተከትሎ ወሎም ሆነ መላው አማራ እንደ አማራ እየተከፈለ ያለው መስዋዕትነት ከባድ ነው ብለዋል። በእጅጉ አሳሳቢ ጭቃኔ የተሞላበት ነው ሲሉ የገለፁት የቡድኑ አውሬያዊ ድርጊትም በራያ አጋምሳ፣ በመርሳ፣ በዳባት ጭና እና በሌሎችም ስለመፈፀሙ አውስተዋል። በሰሜን ወሎ ከሀምሌ 5 ቀን 2013 ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ጦርነት አሁን ላይ ከሁለት ወራት በላይ ሆኖታል ያሉት አስተያት ሰጭዎች በመሆኑም ከተፈናቃለው በመቶ ሽህ የሚቆጠር ህዝብ ባሻገር በወራሪው ቡድን ስር ያለው ወገናችን አደጋ ላይ ነው ብለዋል። አጠቃላይ የሰሜን ወሎ ህዝብ በቡድን መሳሪያ ጭምር በከሃዲው ቡድን ከሚፈፀምበት የገፍ እና የግፍ ግድያ፣መፈናቀልና ዝርፊያ ባሻገር አጠቃላይ የኑሮ ምስቅልቅሎሽ ውስጥ እንደገባ መታወቅ አለበት ሲሉም አክለዋል። የንፁህ መጠጥ ውሃ ባለመኖሩ ማህበረሰቡ ለውሃ ወለድ በሽታ እየተዳረገ ነው፤ ወራሪው ባለበት መድሃኒት እና ባለሙያ ባለመኖሩም የህክምና አገልግሎት ለማግኘት አልተቻለም በመሆኑም በጥይት ከሚገደለው በተጨማሪ በህክምና እጦት የሚሞተው እየጨመረ ስለመሆኑ ገልፀዋል። በተለይ ደግሞ የኤች አይቪ፣የደም ግፊት፣የስኳር፣ የቲቪ እና ሌሎች የእለት ከእለት የባለሙያ ክትትል፣ የወገን ድጋፍንና የመድሃኒት አቅርቦት የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከሚደርሰን የውስጥ መረጃ እንደተረዳነው በስቃይ ህይወታቸው እያለፈ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ልዩ ድጋፍ እና እንክብካቤ ለሚሹ ነፍሰ ጡር እናቶች እና ህጻናት ያሉበት ሁኔታ በእጅጉ ፈታኝ ነው ተብሏል። በአካባቢው የመብራት፣የወፍጮ እና የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩና ዓለም አቀፍ የተራድኦ ተቋማትም ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ድጋፍ እያደረሱ ባለመሆኑ የችግሩን ስፋት አሳሳቢ እንደሚያደርገው ግልፅ ነው ብለዋል። በመሆኑም መንግስት ጦርነቱን በተቻለ ፍጥነት በአሸናፊነት ለማገባደድ ጠንክሮ ካልሰራና ካልቻለ በስተቀር ከዚህ በላይ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ እንደሚደርስ ግልፅ ነው ብለዋል። መንግስት በዘገየ ቁጥር ቡድኑ የሚፈፅመው ግድያ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ ጭቆና፣ አፈና እና የኑሮ ምስቅልቅሉ እንዲቀጥል መፍቀዱ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባዋል ብለዋል። በመጨረሻም መንግስትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የአለም የምግብ ፕሮግራም፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን፣ የቀይ መስቀልና ሌሎች የሀገር ውስጥና የውጭ ተራድኦ ድርጅቶች፣ መላው የአማራ ህዝብና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 Telegram :-https://t.me/asharamedia24 Yotube:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply