በጦርነት ለደረሰ ጉዳት የመድን ሽፋን እንደማይሰጥ ተገለፀ

https://gdb.voanews.com/09410000-0a00-0242-15ac-08daf0258310_tv_w800_h450.jpg

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በጦርነት ምክንያት ለደረሱ ጉዳቶች ካሳ እንደማይሰጥ አስታወቀ፡፡ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ነፃነት የተቋሙ የመድን ውሎች ጦርነትን እንደማይሸፍኑ ተናግረዋል።

ድርጅታቸው ካሳ የሚሰጠው ከጦርነት ውጭ ለደረሱ አደጋዎች ብቻ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

አንድ የዘርፉ ባለሞያ “የመድን ተቋማት በጦርነት ለሚከሰቱ ጉዳቶች የዋስትና ሽፋን የማይሰጡት የካሳ መጠኑ ከመክፈል አቅማቸው በላይ ስለሚሆን ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በሁለት ዓመት ውስጥ በትግራይ ካሉት ደንበኞቹ ሊያገኝ የነበረውን 200 ሚሊዮን ብር የአረቦን ገቢ በጦርነቱ ምክንያት ማጣቱን አቶ ነፃነት ለሜሳ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የትግራይ ቅርንጫፎቹን ዳግም ሥራ ለማስጀመር በቅርቡ የባለሞያዎች ቡድን ወደ ክልሉ እንደሚልክም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

Source: Link to the Post

Leave a Reply