በጦርነት በፈራረሰችው ሶሪያ የጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ ህጻንን ሕይወት ሲቀጥፍ በርካቶችን አፈናቅሏል፡፡

በሐገሪቱ ሰሜን ምዕራብ የጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ ህጻንን ሕይወት ቀጥፏል፡፡ በአስር ሺ የሚቆጠሩ ዜጎችን ደግሞ ከፈራረሰው መኖሪያ መንደራቸው አፈናቅሏ፡፡

በጦርነት ለተጎዳችው ሶሪያ ድጋፍ በማድረግ የሚገኙ ድርጅቶች ናቸው የ6 ኣመቱ ህጻን መሞቱን ያረጋገጡት፡፡በጎርፉ በትንሹ 41 ሺ 200 ሰዎች መፈናቀላቸውን የገለጸው ዘገባው በ169 የመኖሪያ ካምፖች ውስጥ የነበሩ ሰነዶች መውደማቸውንም ጠቁሟል፡፡ አንድ የስምንት ልጆች አባት በውሃ ውስጥ ለመዝናናት ሳይሆን መውጫ አጥተን እየዋኘን ነው ሲል በጭንቀት ለአልጄዚራ ተናግሯል፡፡

በጎርፍ አደጋው የተፈናቀሉ እንዲሁም በጎርፉ የተከበቡ ዜጎችን ለማውጣት ዓለም ዓቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ርብርብ እያደረጉ መሆኑንም ዘገባው ጠቁሟል፡፡

*************************************************************************

ቀን 12/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

ምስል፡- የአሐዱ ሎጎ

The post በጦርነት በፈራረሰችው ሶሪያ የጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ ህጻንን ሕይወት ሲቀጥፍ በርካቶችን አፈናቅሏል፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply