በጫሞ ሐይቅ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ እስካሁን ድረስ የሦስት ሰዎች አስክሬን መገኝቱ ተነገረ፡፡

በትላንትናው እለት በደቡብ ክልል ጫሞ ሐይቅ 8 ሰዎችን ጭና በጉዞ ላይ የነበረች ጀልባ መስጠሟ ተነግሮ ነበር፡፡

በሃይቁ እስካሁ ድረስ በተደረገው የአስከሬን ፍለጋ የሦስት ሰው አስክሬን መገኝቱ ታውቋል፡፡

እስካሁን ባለው ሁኔታ አምስት ነፍስ አደን ጀልባዎች ጨምሮ ሌሎች ዋናተኞች ተሰማርተው ከፍተኛ ፍለጋ ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ወደ አርባምንጭ ከተማ ለመግባት በጉዞ ላይ ከነበሩ ስምንቱ ሰዎች በተጨማሪ እቃ ጭና እንደነበር የተነገረላት ጀልባ በክብደት ምክንያት ሳትሰጥም እንዳልቀረች የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበዉ አዳል ተናግረዋል።

የተቀሩትን አምስት ሰዎች አስክሬን እስካሁን ማግኘት እንዳልተቻለ የተናገሩት የፖሊስ አዛዡ ፖሊስ ከከተማዉ ወጣቶች ጋር በመሆን የግለሰብ ጀልባዎችን ጭምር ተጠቅሞ የሟቾችን አስክሬን በማፈላለግ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply