በጫንጮ ከተማ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ “ሪሪ ኤስ.ፒ ሲ” የወለል ንጣፍና ዘኮሎ ማምረቻ ፋብሪካ ስራ ተጠናቆ ስራውን በይፋ ጀምሯል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በጫንጮ ከተማ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በ8 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን 390 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ ፋብሪካው ሚድሮክ የግንባታ ዕቃዎችን በአገር ውስጥ ለማምረት አቅዶ ወደ ሥራ ከገባባቸው ዘርፎች መካከል ተጠቃሽ ነው።
ይህም በአገሪቱ ያለውን የኮንስትራክሽን ግብዓት ፍላጎት ለመሙላት እንደሚያግዝ ነው አቶ ጀማል የገለጹት፡፡
የፋብሪካው አጠቃላይ የግንባታ ሥራ በ6 ወራት ውስጥ መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን ፋብሪካው እጅግ ዘመናዊ እና ዓለም የደረሰባቸው ቴክኖሎጂዎች የተገጠመለት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ድርጅቱ ወደ ሥራ ያስገባው የወለል ንጣፍና ዘኮሎ ማምረቻ ፋብሪካ ለአገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ግብዓት በማቅረብ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ተብሏል፡፡
አቶ ጀማል እንዳሉት ሚድሮክ በግብርናው፣ በማዕድን፣በሆቴልና ሆስፒታሊቲ እንዲሁም በግንባታ ዘርፍ ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፎቶ፡-ኢዜአ
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video