በጭና በአሸባሪው ሕወሓት የተገደሉ ንፁሃን 200 መድረሱን የዐይን እማኞች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጭና ቀበሌ በአ…

በጭና በአሸባሪው ሕወሓት የተገደሉ ንፁሃን 200 መድረሱን የዐይን እማኞች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጭና ቀበሌ በአሸባሪው ሕወሓት የተገደሉ ንፁሃን ቁጥር 200 መድረሱን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ የዓይን እማኞቹ እንደሚናገሩት ጭና ቀበሌ ዳግማዊ ማይካድራ ሆናለች፤ በጭና ሚካኤል አቅራቢያ 59 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በጅምላ ተቀብረዋል። ከአንድ ቤተሰብ እስከ 6 የሚሆኑ የቤተሰብ አባላት መሞታቸውንም ተናግረዋል። አሁን ላይ የሟቾች ቁጥር ከመብዛቱ የተነሣ ቀብር ለማከናወን መቸገራቸውንም ነዋሪዎቹ ለኢቢሲ ገልጸዋል። የዓይን እማኞች እንዳረጋገጡት የአሸባሪ ቡድኑ ታጣቂዎች የካህናት ሚስቶችን እና ልጃገረዶችን ደፍረዋል፤ እንስሳትን ሳይቀር በጭካኔ ገድለዋል፤ ንፁሃንን አሰልፈው በጥይት ፈጅተዋል፤ በየቤቱ እየዞሩ ሀብት እና ንብረት ዘርፈዋል የቀረውን አውድመዋል ሲል ዋልታ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply