በፈረንሳይ ፓሪስ የተካሔደ ውይይት ሐማስ ታጋቾችን እንዲለቅ እና በጋዛ ተኩስ እንዲቆም ሊያደርግ ወደሚችል ሥምምነት ሊያመራ እንደሚችል “መግባባት” መኖሩን አሜሪካ አስታወቀች።በፓሪስ በተካሔደ…

በፈረንሳይ ፓሪስ የተካሔደ ውይይት ሐማስ ታጋቾችን እንዲለቅ እና በጋዛ ተኩስ እንዲቆም ሊያደርግ ወደሚችል ሥምምነት ሊያመራ እንደሚችል “መግባባት” መኖሩን አሜሪካ አስታወቀች።

በፓሪስ በተካሔደው ውይይት የእስራኤል፣ አሜሪካ፣ ግብጽ እና ቃጣር ተወካዮች መገኘታቸውን የገለጹት የአሜሪካ ብሔራዊ ደሕንነት አማካሪ ጄክ ሱሉቫን ተኩስ አቁሙ እና ታጋቾች የሚለቀቁበት ሁኔታ ምን አይነት እንደሚሆን በአራቱ መካከል መግባባት መኖሩን ተናግረዋል።

በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ገና ድርድር እየተካሔደ መሆኑን የገለጹት ጄክ ሱሊቫን ግብጽ እና ቃጣር ከሐማስ እንደሚወያዩ ተናግረዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ግን እየተካሔደ የሚገኘው ውይይት ታጋቾችን የሚያስለቅቅ ሥምምነት ላይ ለመድረሱ እርግጠኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። የእስራኤል የጦርነት ጊዜ ካቢኔ ትላንት ቅዳሜ ተደራዳሪዎች ወደ ቃጣር ለመላክ መወሰኑን አስታውቋል።

ወደ ተኩስ አቁም ሊመራ ይችላል የተባለው ውይይት እየተደረገ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የእስራኤልን ጦር ወደ ራፋ ለማዝመት በያዙት ዕቅድ እንደጸኑ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይኸንንው ዕቅዳቸውን በሚቀጥለው ሣምንት ለእስራኤል የጦርነት ጊዜ ካቢኔ እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጋዛ ሠርጥ የእስራኤል እና የሐማስ ውጊያ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 29 ሺሕ 692 መድረሱን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ዛሬ እሁድ አስታውቋል።

በውጊያው 69 ሺሕ 879 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። በጋዛ ጤና ሚኒስቴር መረጃ መሠረት ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 86 ሰዎች ተገድለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply