በፋኖ አስር አለቃ መዝገቡ ዋሌ ስም የተደራጁ የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፋኖ አባላት በዛሬው እለት ተመርቀዋል። ባህርዳር:- ሚያዚያ 27/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በርካ…

በፋኖ አስር አለቃ መዝገቡ ዋሌ ስም የተደራጁ የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፋኖ አባላት በዛሬው እለት ተመርቀዋል። ባህርዳር:- ሚያዚያ 27/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በርካታ አባላቱን ሲያሰለጥን የቆየው የሞጣ እና አካባቢው የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፋኖ በዛሬው እለት በጎድር ሜደ ቀበሌ የምረቃ ስነስረሀት አካሂደዋል።በምረቃ ፖሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የሞጣ እና አካባቢው የፋኖ አደረጃጀት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ክንፈ መላክ ካሳ እንደገለፁት ፋኖ ሊባ ዘራፊ ነው የሚባለው አሉባልታ ከእውነታ የራቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል።አክለውም ፋኖ የሚደራጀው የሚሰለጥነው አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ለማዳን ነው እንጂ የተለየ ተልዕኮ ኑሮት አይደለም: የፋኖ አስር አለቃ መዝገቡ ዋሌ ራዕይን ለማስቀጠል ሁሉም ወጣት ሊረባረብ ይገባል ብለዋል።በመጨረሻም የትኛውም የህብረተሰብ ክፍል ፋኖን በመደገፍ የበኩሉን አስተዋፅ እንዲወጣ የመድረኩ ተሳታፊዎች ለአሻራ ሚዲያ ገልፀዋል ። ሙሉ ዝግጅቱን በአሻራ ሚዲያ ዩትዩብ ቻናል ይከታተሉን ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply