በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናት መብቶች በተሻለ ሁኔታ እንዲከበሩ እየተሰራ መሆኑ ተነገረ፡፡

በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ የሚያልፉ ህጻናት መብቶቻቸው በተሻለ ሁኔታ እንዲከበሩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በትስስር እየተሰራ እንደሚገኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ተኽሊት ይመስል ገልፀዋል፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት እና በሴቶችና ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር በቅንጅት ፍትህ ለህጻናት ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ የህግ አገልግሎትን በክፍያ ለማግኘት አቅም የሌላቸው ህጻናት ተገቢውን የህግ እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊና ስነልቦናዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ይሰራል፡፡

ሁለንተናዊ መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር የስራ ትስስር በማድረግ ህጻናትና ቤተሰቦቻቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመደረግ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡ የህጻናት ጥቅምና ደህንነትን ከማስቀደም አንጻር ህጻናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜ ሁሉም የመንግስታዊ ወይም የበጎ አድራጎት ተቋማት እንዲሁም ፍርድ ቤቶችና የአስተዳደር አካላት በሚወስዷቸው ውሳኔዎችና እርምጃዎች የህጻናት ጥቅምና ደህንነት በቀዳሚነት መታሰብ እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡

ህግ አውጪ አካላትም በሚያውጧቸው ህጎች  ለህጻናት ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸውም ነው ያሳሰቡት።

ዘጋቢ እየሩሳሌም ብርሃኑ

ቀን 22/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply