You are currently viewing “በፍትሕ ሥርዓቱ አፈና ተፈፅሞብኛል” ጋዜጠኛ ገነት አስማማው! ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ “…. በማንነቴ ከደረሰብኝ ጥቃት በተጨማሪም በሴትነቴ ላይ የደረሰብኝ ጾታዊ…

“በፍትሕ ሥርዓቱ አፈና ተፈፅሞብኛል” ጋዜጠኛ ገነት አስማማው! ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ “…. በማንነቴ ከደረሰብኝ ጥቃት በተጨማሪም በሴትነቴ ላይ የደረሰብኝ ጾታዊ…

“በፍትሕ ሥርዓቱ አፈና ተፈፅሞብኛል” ጋዜጠኛ ገነት አስማማው! ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ “…. በማንነቴ ከደረሰብኝ ጥቃት በተጨማሪም በሴትነቴ ላይ የደረሰብኝ ጾታዊ ትንኮሳ እንዳለ ለፍርድ ቤቱ በአፅንዖት አቤቱታ ባቅርብም ፍ/ቤቱ የተፈፀመብኝን ነውር ችላ ብሎ እያለፈብኝ ነው” በማለት ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ችሎት መናገሯ ተሰምቷል። ጋዜጠኛ ገነት አስማማው በአማራነቷ ደረሰብኝ ካለችው በግፍ መታፈን በሗላ፣ በአፈኗት ነውረኛ የዐብይ አህመድ ወታደሮች ወሲባዊ ትንኮሳ እንደተፈፀመባት ችሎት በቀረበችበት ቀን ሁሉ ለማስረዳት ሞክራ እንደነበርና ነገር ግን ችሎቱ ላይ የተሰየሙት ዳኛዎችም ድርጊቱን እንደተራ ጉዳይ አቃለውት እንዳለፉም ገልጻለች። “ይህን የችሎት ውሎ እና የተፈፀመብኝን ድርጊት ለማጋለጥ በችሎቱ የሚታደም ነፃ ጋዜጠኛ አለመኖር ደግሞ ሌላው ሳንካ ሆኗል” ያለችው ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፤ በጋዜጠኞች ቅሬታ እንዳላትም ተናግራለች፡፡ በችሎት የነበሩ ክርክሮችና አቤቱታዎች በተገቢ የማይዘገቡና፣ መንግስት ለራሱ አመች በሆነ አቀራረብ ለፕሮፖጋንዳ ከሚያውለው ግራና ቀኝ ክርክርን ጭብጥ ያላማከለ መረጃ በቀር የእኛ ድምፅ እየተሰማ አይደለም ስትል ተናግራለች። ነፃ እና ገለልተኛ የሆኑ ሚዲያዎች እና ጋዜጠኞች በችሎት ተገኝተው በመዘገብ ለህዝባችን መረጃ አንዲያቀርቡ ስትል ጥሪ አድርጋለች፡፡ ችሎቱ ክፍት ሆኖ ሳለ፤ አንዳች ነፃ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ወኪል በችሎት አለመገኘት አስደንጋጭ ነውም ብላለች፡፡ ድል ለአማራ !! #AmharaStruggle #Justice4Amhara #AmharaGenocide “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply