በፍቼ ከተማ ከ2ዐ ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ይዞ ለመገበያየት የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

በፍቼ ከተማ ከ2ዐ ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ይዞ ለመገበያየት የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በፍቼ ከተማ 2ዐ ሺህ 800 ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ይዞ ለመገበያየት የሞከረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ ኢንስፔክተር መላኩ ቶላ ለኢዜአ እንደገለጹት ትላንት በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ ግለሰብ በከተማው የቀበሌ ዐ4 ነዋሪ ነው።
በከተማው በአብዮት ፍሬ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኝ የማገዶ እንጨት በሀሰተኛ የብር ኖት ለመገበያየት ሲሞክር በሕብረተሰብ ጥቆማ ቁጥጥር ሥር መዋሉን ተናግረዋል።
በፍቼ ከተማ በከብት ድለላ ሥራ ላይ የተሰማራው ተጠርጣሪው ግለሰብ በእጁ ላይ የተገኙትን ሀሰተኛ የብር ኖቶች “ሰንጋ ሳሻሽጥ ከገዢው ላይ የተቀበልኩት ነው” ሲል መናገሩን ጠቁመዋል።
ድርጊቱ ቀደም ሲል በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች ከተያዙት የብር ኖቶች ጋር ተያያዥነት ሊኖረው ስለሚችል ፖሊስ ሁኔታውን ከባንክ ባለሙያዎች ጋር እያጣራ መሆኑን ተናግረዋል።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ወሎ ጉዳዩን ለህግ ለማቅረብ በምርመራ ላይ መሆኑንም ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል።
በዞኑ የእህልና የከብት ንግድ በሚከናወንባቸው አካባቢዎች ሀሰተኛ የብር ኖቶች ዝውውር እንዳለ የሚጠቁሙ ምልክቶች እንዳሉ የገለጹት ኢንስፔክተር መላኩ ሕብረተሰቡ በተለይም በገና በዓል ግብይት በመሰል ወንጀል እንዳይታለል ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በፍቼ ከተማ ከ2ዐ ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ይዞ ለመገበያየት የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply