በትግራይ የተካሄደውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ አመራሮቹ በሕግ እየተፈለጉ የሚገኙት የህወሓት ጉዳይ በቅርቡ ከሚካሄደው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ጋር የሚታይ መሆኑን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሶልያና ሽመልስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በዚህ ዓመት ሊካሄድ ከታቀደው ምርጫ በፊት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እንደ አዲስ የሚታይ ስለሚሆን የህወሓት ጉዳይም አብሮ እንደሚታይ አመልክተዋል።
Source: Link to the Post