በፓኪስታን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ከ500 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡በደቡባዊ ፓኪስታን የሙቀት መጠኑ መጨመሩን ተከትሎ በስድስት ቀናት ውስጥ ከ500 በላይ ዜጎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/gnPyDFBFor3CLJwGUctdI3VMDp0dZZbiA70qSpsoVVgpdZWiQvjIAUaSeBLQfpfhTPFwKIrvGtxYsPkNUwAXEUmvK7gGjp0Iq9mkpJzcAdUi8VB3o949-wMMxWdDKdpmcgwedrlUHObTuVL_r7BstgIOjqNCJV5vwUtmUSUhdv19xRCyD1QhEhOGCggIk5H8xie3OZaamaFvmMZ4TVV_DXxWI5oTd-Z-tQZDTUGSHpaqfr9nq2EkZadtJe4nMQVnS7UGLKZZECoM-BTKDFFsnR3_Gn-BYU8fPuI0RegL1pYdsuI8VC_SRPQiwglRwrG2yJL5KFLFV3L0XEZkcThO3Q.jpg

በፓኪስታን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ከ500 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በደቡባዊ ፓኪስታን የሙቀት መጠኑ መጨመሩን ተከትሎ በስድስት ቀናት ውስጥ ከ500 በላይ ዜጎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡

በየቀኑ ከ30 እስከ 40 ሰዎችን ወደ ካራቺ ከተማ አስከሬን ክፍል እንደሚወሰድ የኢዲሂ አምቡላንስ አገልግሎት መረጃ አመልክቷል።

በሀገሪቱ በተከሰተ ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ባለፉት ስድስት ቀናት ውስጥ 568 ያህል አስከሬን እየሰበሰበ ሲሆን ከዚህም አሃዝ ውስጥ 141 የሚሆነው በማክሰኞ ዕለት ብቻ መሆኑም ተጠቁሟል።

በካራቺ ሲቪል ሆስፒታል ከእሁድ እስከ እሮብ ባሉት ቀናት መካከል በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ችግር የገጠማቸው 267 ሰዎችን እንደተቀበለ የድንገተኛ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ኢምራን ሳርዋር ሼክ ገልፀዋል።
ከእነዚህ ውስጥ ግን የ12ቱ ህይወት ማለፉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply