በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ሮቢ ንግላንዴ በ33ኛው ደቂቃ ፣ ጌታነህ ከበደ በፍጹም ቅጣት ምትና በጨዋታ በ39ኛ እና 43ኛው ደቂቃዎች ላይ እና ዳዊት ታደሰ በ55ኛው ደቂቃ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥረዋል።

የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ እና የማስተዛዘኛ ጎል ብሩክ በየነ በፍፁም ቅጣት ምት በ80ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል።

 

The post በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply