#በ 1ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ አላለፈም ተባለ! ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስ…

#በ 1ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ አላለፈም ተባለ! ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል። ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተኑ 2 ሺህ 959 የመደበኛ ትምህርት ቤቶች መካከል 1 ሺህ 161 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪዎችን እንዳላሰለፉ አስታውቀዋል፡፡ በውጤቱ መሰረት ከአጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 798 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ ያሳለፉ መሆኑ ታውቋል፡፡ 7 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ ያሳለፉ ሲሆን እነዚህም ትምህርት ቤቶች ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ ቤት፣ ኦዳ አዳሪ ልዩ ት/ቤት ፣ ባህርዳር ስቴም ት/ቤት ፣ ወላይታ ሊቃ ት/ቤት፤ የጎንደር ማህበረሰብ አቀፍ ት/ቤት እና ከግል ትምህርት ቤት ደግሞ ለባዊ ት/ቤት መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በጋራ እንደ አገር በትምህርቱ ዘርፍ ወድቀናል ያሉት ሚኒስትሩ ውድቀታችንን አርመን የተሻለ የትምህርት ስርአትን ለመዘርጋት መስራት አለብን ብለዋል፡፡ የተሻለ ትውልድን ለመፍጠር በተማሪዎች፣ በወላጆች እና በማህበረሰቡ እንዲሁም በመንግስት ኃላፊነት ተወስዶ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል።የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት – በተማሪዎች ውጤትም ሆነ በትምህርት ቤት ደረጃ በተመዘገበው ውጤትየደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ከሀገር አቀፍ አንደኛ መሆኑን ትምህርት ሚኒስትር አስታውቋል! በትምህርት ቤቱ አጠቃላይ የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት- 69 ሲሆን እስካሁን የ68ቱ ተማሪዎች ውጤታየው ታውቋል፡፡ በዚህም መሠረት የተማሪዎቹ ዝርዝር ውጤት፦ ~ 25 ተማሪዎች – ከ600 በላይ ~ 40 ተማሪዎች – ከ 500 – 599 ~ 3 ተማሪዎች 450-499 ማስመዝገባቸው ታውቋል፡፡ ውጤቱ ያልታወቀው የአንድ ተማሪ ብቻ ነው። በቅርብ ጊዜ ትልቅ ራዕይን ሰንቆ እውን በተደረገና ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ከኮቪድ በኃላ ፥ ለረዥም ጊዜ በጦርነት ውስጥ በቆየውና ብዙ ውድመት ባስተናገደ አዳሪ ት/ቤት ይህን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ይህን ትምህርት ቤት ማሳደግና ማጎልበት ብሎም ማስፋፋት ለወደፊቱ የሀገር ተረካቢ የሚሆኑ ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል የተገኘው ውጤት በቂ ማሳያ ነው ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply