በ2012 ዓ/ም  ከተተከሉ ችግኞች 80 በመቶ ውጤታማ ጽድቀት ማሳየታቸው ተነገረ፡፡

ለአራት ተከታታይ ዓመታት ተግባራዊ እንደሚደረግ የተነገረለት የችግኝ ተከላ ፕሮጀክት ከ2019 እስከ 2022 ድረስ እንደሚቀጥል የተነገረ ሲሆን የችግኞቹን የእድገት ሁኔታ ለማወቅ ባለፈው ዓመት በተደረገ ጥናታዊ ዳሰሳ የጽድቀት መጠናቸው አመርቂ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በ2022 ዓ/ም 20 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል እቅድ እንደተያዘ በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጋሻው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ አምና ከተተከሉ ችግኞች ውስጥም 80 በመቶ የሚሆኑት ውጤታማ ጽድቀት አሳይተዋል ብለዋል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ከተደረገው ዳሰሳ በኋላ ለቀጣዩ ዳሰሳ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

******************************************************************************

ዘጋቢ፡እየሩሳሌም ብርሃኑ

ቀን 22/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply