በ2015 በጀት አመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለት ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።የግድቡን ቀሪ ግንባታ ለማከናወን ለሚያ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/J8qDZZYEFtHQffBJ-MTR1fVLFp8S8D5iKv8ODlu7lfEeKM1nZ9FknmXNgkMiiTxlH8XA80--Y6CUw6r5R1n_x-Jbs0OGWwvYyQjlDtBe4SAoNZUdfoUyO4fZYCqXeUmWP3yP96UlH2sgmVGPHIr4nHSsaV-Yik-9I86xxkt8s3NytxoUnolbLuIQKwsaLoVuBppz2lP26hfAZKsp2oEBj5SMsqtOItMpOqkMq_ePRs9iVA9Wz-rb8b8DQ3ObBXhQkO2BOQu611dAQXx1FcOsGxi6drIGz9xyXT1M5g5H4Bbd9Ac_nn9gwtEUnltbmcxhgdDGKby-7nRya98HAjL3iw.jpg

በ2015 በጀት አመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለት ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የግድቡን ቀሪ ግንባታ ለማከናወን ለሚያስፈልገው ተጨማሪ 60 ቢሊየን ብር የህዝብ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤውን ትናንት አካሂዷል።

የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታገል ቀኑብህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያውያን እውቀትና ገንዘብ እየተገነባ የሚገኘው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ታላላቅ ስኬቶችን አስመዝግቧል።

በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለግድቡ እያደረጉት ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ጠቅሰዋል።

በሃብት ማሰባሰብ በኩል በ2014 በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 18 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸው፤ በተያዘው 2015 በጀት ዓመት 2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ሰምተናል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጳጉሜ 04 ቀን 2014 ዓ.ም

ለወቅታዊና ታማኝ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናላችንን ይከታተሉን!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply