የአዲስ አበባ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ መኳንንት ምናሴ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት፣ጥፋት የተገኘባቸው አሽከርካሪዎች ተገቢው እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው።
ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑ የትራፊክ አደጋዎች በአሽከርካሪዎች የሚደርሱ መሆኑን የተናገሩት ተወካዩ፣ ለአብነትም ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር፣ ጠጥቶ በማሸከርከር እና የትራፊክ ህግን የተላለፉ አሽከርካሪዎች ሊቀጡ ችለዋል ብለዋል።
አክለውም የትራፊክ ቅጣት ላይ ማሻሻያዎችን ለማድግ ጥናቶች እየተካሔዲ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
በእሌኒ ግዛቸው
ጥቅምት 09 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post