በ2023 ዓ.ም ብቻ 1.1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአውሮፓ ህብረት ጥገኝነት መጠየቃቸው ተገለፀ፡፡

የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ከዚህ ቀድም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ ስደተኞችን ከተቀበሉበት ከ2015 እስከ 2016 ከነበረው በላይ በ2023 ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጥገኝነት ጠያቂዎችን ማስተናገዱ ተገልፃል፡፡

እ.ኤ.አ በ2023 ብቻ ከ1.14 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለአውሮፓ ህብረት ጥገኝነት መጠየቃቸውን የጥገኝነት ኤጀንሲ /EUAA/ ማክሰኞ ዕለት በወጣው ሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል፡፡

መረጃው ህብረቱ እየጨመረ የመጣው ጦርነትና ያለው ጫና የብሄር ፖለቲካን ይበልጥ እንዳይጨምረው ያሰጋል ብሏል፡፡
የ2023 አሃዝ እንደሚያሳየው ከሆነ ካላፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር 18 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

1.3 ከዚያም 1.9 ሚሊዮን ሰዎች በአውሮፓ ህብረት የተጠለሉበት አሃዝ ከ2015 እና 16 ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ነው ሲል ዘገበው ያሳያል፡፡

ባለፈው ዓመት የጥገኛ ጠያቂዎች ቁጥር አንድ መዳረሻ ጀርመን መሆኗም የተገለፀ ሲሆን ሶሪያ እና አፍጋኒስታን ደግሞ ከፍተኛ ጥገኝነት ጠያቂ ሀገራት መሆናቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply