You are currently viewing በ37 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በተካሄደ የኦዲት ምርመራ፤ “ምንም ጉድለት” ያልተገኘባቸው ሁለቱ ብቻ መሆናቸው ተገለጸ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)    ግንቦት 16/2015 ዓ/ም…

በ37 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በተካሄደ የኦዲት ምርመራ፤ “ምንም ጉድለት” ያልተገኘባቸው ሁለቱ ብቻ መሆናቸው ተገለጸ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 16/2015 ዓ/ም…

በ37 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በተካሄደ የኦዲት ምርመራ፤ “ምንም ጉድለት” ያልተገኘባቸው ሁለቱ ብቻ መሆናቸው ተገለጸ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 16/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የ2013 ሂሳባቸው ኦዲት ከተደረጉ 37 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ “ምንም ጉድለት ያልተገኘባቸው” ሁለቱ ብቻ እንደሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጧል። ሚኒስቴሩ ኦዲት ከተደረጉት ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ 48.6 በመቶው “ተቀባይነት የሚያሳጣ” ደረጃ ላይ እንደሆኑ ተረጋግጧል ብሏል። የትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያስታወቀው ትላንት ማክሰኞ ግንቦት 15፤ 2015 በተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው። በዚህ ስብሰባ ላይ በቀረበው የሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከተነሱ ጉዳዮች ውስጥ፤ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን የተመለከተው ይገኝበታል። ዩኒቨርስቲዎቹ ዘንድሮ ያስተናገዷቸውን ተማሪዎች ብዛት፣ በፓርላማ ለመጽደቅ በሂደት ላይ ያለው የዩኒቨርስቲዎች ራስ ገዝ አስተዳደር አዋጅ እና በዚህ ዓመት የሚጀመረው የተማሪዎች መውጫ ፈተና በሪፖርቱ የተጠቀሱ ጉዳዮች ናቸው። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ያላቸው የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትም በዚሁ ሪፖርት ተካትቷል። ሪፖርቱን ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት በንባብ ያቀረቡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ ተቋማቱ በዚህ ረገድ ያሉበት ደረጃ የፌደራል ዋና ኦዲተር ካደረገው የ2013 ዓ.ም የሂሳብ ኦዲት በኋላ ለመለየት መቻሉን አስታውቀዋል። እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ ኦዲት ከተከናወነባቸው 37 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ 18 ያህሉ “ተቀባይነት የሚያሳጣ” የኦዲት ጉድለት ተገኝቶባቸዋል ሲል የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply