በ40 ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለለት የገዳ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታዉ መጀመሩ ተነገረ::

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ሞቱማ ተመስገን በተለያዩ ምዕራፎች የተከፋፈለ የነፃ ንግድ፣ የወጪ ንግድ፣ የመዝናኛና የኢንዱስትሪ ከተማ ግንባታ ተጀምሯል ብለዋል፡፡

አቶ ሞቱማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ማቋቋም ለዜጎች የሥራ እድል ከመፍጠሩ ባሻገር ተጨማሪ ምርትና አገልግሎት እንዲኖር ያስችላል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያም የአፍሪካ የነፃ የንግድ ቀጣና አባል እንደመሆኗ መጠን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማቋቋሟ ከቀጣናው ገበያ የሚገባትን እንድታገኝ ያስችላታልም ብለዋል፡፡

በመሆኑም ባለስልጣኑ አቶ ሞቱማ በአምስት ዓመታት ውስጥ ዝግጅቱ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው 3ሺህ 1 መቶ 50 ሔክታር መሬትን የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለመስራትና ምቹ አድርጎ ለአልሚዎች ለመስጠት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በመጀመሪያው ዙር የመሠረተ ልማት ከተዘጋጀ በኋላ የአገር ውስጥና የውጭ አልሚዎችና ኢንተርፕራይዞች ዞኑ ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

አሁን ባለው የገበያ ሁኔታ ለቦታው ውሃ ፣መብራት፣መንገድ እንዲሁም ቦታውን ለስራ ምቹ ለማረግና ለማልማት ከ ከ60 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተብሏል

በልዉል ወልዴ

መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply