በ50ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነአርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 17 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/I0njxX1eOJ2x9ejrvhsL5Dur6npN_cYadawvrRhLPqUuT6tzESjcy4fe_lF5SlfwM-O413Mx-gELb6PFVVcADIWLHZXDsoF2bXeQr-AcAXFO_T0YKDil30SCecZyvnRVlVZ_HLICTrSkAFE80kjpkAtVUtp-xw6wUHpaIZhL87V_uhFEkxWAJaeKJko8MoznxB7QUVjCIGXSzYp_2yVB782VomHWMYYC8HwpBFZxHA0Zdo_kop8n2NVwcXeygqkc9bsVBLG9L_plx1Eu0ewIophtzGpJmR_u-Y7kPtPnf2usNRovGrc6Td5LDIigzSNWoVpHy48EAmqwXDW2V1PLFg.jpg

በ50ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ

አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 17 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ፈቀደ።

ግለሰቦቹ የታሰሩት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር” በመንቀሳቀስ በሚል ነበር፡፡

ዛሬ በጉዳዩ ላይ ብያኔ ለመስጠት የተሰየመው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ በመዝገቡ ከተካተቱት 20 ተጠርጣሪዎች ውስጥ አስራ ሰባቱ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ያሬድ ገብረፃዲቅ በማኅበራዊ ሚዲያ ስሙ ያያ ዘልደታ፣ ፍስሃ እያዩ እና ጌትነት ታከለ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ግን 11 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንደተፈቀደባቸው ጠበቃ አያሌው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply