በ55 የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረከደንበኞች የደረሰው ቅሬታ መሰረት በማድረግ እንዲሁም አገልግሎቱ ባከናወነው የስራ ክትትል ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ…

በ55 የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ

ከደንበኞች የደረሰው ቅሬታ መሰረት በማድረግ እንዲሁም አገልግሎቱ ባከናወነው የስራ ክትትል ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ስራ ማሰናበት የሚደርስ እርምጃ በሰራተኞች ላይ መውሰዱን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በአገልግሎቱ 13 ሰራኞች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ በ35 ሰራተኞች ላይ ከ7 እስከ 90 ቀን የሚቆይ የደሞዝ ቅጣት እንዲሁም በ5ቱ ላይ ከስራ የማሰናት እርምጃ እንደተወሰደ የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ዩሃንስ ገብሬ ተናግረዋል፡፡

በዋናነት ሙስና እንደ አንድ ምክንያት የሚጠቀስ መሆኑንእና እሚጠበቅባቸውን አገልግሎት በወቅቱ ባለማከናወን እርምጃ እንደተወሰደ ተመላክቷል፡፡

በተደጋጋሚ የጽሁፍ እና የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸው ባልታረሙ የአገልግሎቱ ሰራተኞች ላይ በማስረጃ በቀረቡ የስራ ስህተቶች እርምጃ እንደወሰደ ተነግሯል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply